Saturday, 07 September 2019 00:00

‹‹የማይሰበረው ኤርሚያስ አመልጋ›› መጽሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


         ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በደራሲና ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው በተፃፈውና በኢትዮጵያዊው ሥራ ፈጣሪና ኢኮኖሚስት ኤርሚያስ አመልጋ ሕይወትና ሥራ ዙሪያ በሚያጠነጥነው ‹‹የማይሰበረው ኤርሚያስ አመልጋ›› መጽሐፍ ላይ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የስነ ጽሑፍና ፎክሎር መምህር ገዛኸኝ ፀጋው (ዶ/ር) ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ እንደሚመራ ታውቋል፡፡ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡

Read 866 times