Saturday, 17 August 2019 13:35

“ከሰንጋተራ እስከ አምስተርዳም” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የተማሪውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ ሆላንድ አገር ከተሰደዱትና ጥገኝነት ከጠየቁት የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን አንዱ በሆኑት መላኩ ተገኝ (ዶ/ር) የተፃፈው “ከሰንጋተራ እስከ አምስተርዳም” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
ፀሐፊው በዋናነነት ከተወለዱበት ሰንጋ ተራ እና አካባቢዋ ጀምሮ አዲስ አበባ ምን ትመስል እንደነበር የልጅነት ጊዜያቸውን የተረኩበትና በትውስታ ዘውግ የሚመደብ የአፃፃፍ ሁኔታን መከተሉም ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የፓኖስ ኢትዮጵያ ይሬክተር የነበሩት ደራሲው መላኩ ተገኝ (ዶ/ር) በመጽሐፋቸው በውጭ አገር የተማሪ እንቅስቃሴና የኢህአፓ ምስረታ ላይ የነበራቸውን ሚና ጨምሮ የኢህአፓን የትጥቅ ትግል አስመልክቶ በሱዳን በአርማጭሆና በጭልጋ የነበራቸውን የመሪነት ሚናና ሌሎችንም ጉዳዮች በስፋት ይዳሰሳል፡፡  በ300 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ192 ብር ከ69 ሳንቲም እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2526 times