Saturday, 17 August 2019 13:16

ሩብ ያህሉ የአለማችን ህዝብ ለውሃ እጥረት ተጋልጧል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከአጠቃላዩ የአለማችን ህዝብ ሩብ ያህል ወይም 1.8 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለውሃ እጥረት ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን አንድ አለማቀፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ወርልድ ሪሶርስስ ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም ሰሞኑን ይፋ ያደረገውን ሪፖርት ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፤ 17 የአለማችን አገራት እጅግ ለከፋ የውሃ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን፣ 44 አገራት ደግሞ ለከፍተኛ የውሃ እጥረት ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡
የውሃ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚታይባቸው 17 የአለማችን አገራት መካከል 12ቱ በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ የሚገኙ መሆናቸውን ያስታወቀው ሪፖርቱ፤እጅግ የከፋው የውሃ እጥረት ያጋጠማት የአለማችን ቀዳሚዋ አገር ኳታር ናት ብሏል፡፡ እስራኤል፣ ሊባኖስ፣ ኢራን፣ ዮርዳኖስ፣ ሊቢያ፣ ኩዌት፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኤርትራና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ እጅግ ለከፋ የውሃ እጥረት በመጋለጥ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከሁለተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ የአለማችን አገራት መሆናቸውንም ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

Read 995 times