Print this page
Wednesday, 14 August 2019 10:33

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(9 votes)

ማዘዝ ቁልቁለቱ
‹‹… ብረር ስልህ ብረር
ስበር ስልህ ስበር
ተኩስ ስልህ ተኩስ
ግደል ስልህ ግደል
ለሙሴ የተሰጠሁ
አሮን የተረከኝ
የኦሪት ሕግ ነኝ
ሀዲስ የማያውቀኝ?
(ለአንዳንድ አለቆች)
ከፈለቀ አበበ ‹‹ብርሃን እና ጥላ››
* * * * * *
ሀገርህ ናት በቃ!
ይቺው እናት ኢትዮጵያ… ሀገርህ ናት በቃ!
በዚህች ንፍቀ ክበብ፤ አይምሽ እንጂ መሽቶ፣
ማታው ከጠረቃ
የነቃም አይተኛ የተኛም አይነቃ፡፡
ይህቺው ናት ዓለምህ ብቻዋን የተኛች ከዓለም
ተደብቃ!!
አኪሯ ቀዝቅዞ ‹‹ያንቀላፋች ውቢት›› ያንተው
የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ፤ ወይ አብረሃት ንቃ!!
(ለማትጠገብ አገርና ለልብ አውልቆች)
ከነቢይ መኮንን ‹‹ጥቁር ነጭ ግራጫ››

Read 2972 times
Administrator

Latest from Administrator