Saturday, 10 August 2019 00:00

ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎችና በምርጫ ሕጉ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

ኢዜማ የተሻሻለው ሕግ እንከን የለሽ ነው ብሏል

             ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የምርጫ ረቂቅ ሕግ ላይ ሰሞኑን ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን ኢዜማ በበኩሉ፤ ሕጉ ተገቢነት ያለውና እንከን የለሽ፤ ነው ብሏል፡፡
ፓርቲዎች በዋናነት ቅሬታ ከሚያቀርቡባቸው ጉዳዮች አንዱ የምርጫ ሕጉ ለምን አልተቀየረም የሚል መሆኑን የጠቆመው ቦርዱ፤ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ሕገ መንግስቱ መሻሻል ያስፈልገዋል ብሏል። - ሕገ መንግስቱ ሳይሻሻል የምርጫ ሥርዓቱን መለወጥ እንደማይቻል በመግለጽ፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ሲመሰረቱ 10 ሺህ፣ በክልል ደረጃ 4ሺ የድጋፍ ድምጽ እንዲያቀርቡ በሕጉ የተደነገገውም ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለመፍጠር በማለም ነው ያለው ቦርዱ፤ ጉዳዩ ከአገሪቱ ሕዝብ ቁጥርና ፓርቲዎች ከሚወክሉት ሕዝብ አንጻር መታየት እንዳለበት አብራርቷል፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች ለምርጫ ውድድር ሲቀርቡ ለጊዜው ከስራ ገበታቸው ያለደሞዝ  ይለቃሉ የሚለው ሕግ የተረቀቀውም፤ የመንግሥት ሥራን ከፓርቲ ሥራ ለመለየት ታቅዶ መሆኑን የገለፀው ቦርዱ፤ አሁን የፓርቲዎችን ቅሬታ በመቀበል እጩ ተወዳዳሪ የመንግስት ሠራተኞች እስከ ሁለት አመት የሚደርስ የአመት ፈቃዳቸውን እንዲጠቀሙና ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሚል መሻሻሉን አስታውቋል፡፡
ምርጫው እንዳበቃም እጩዎች ወደ መደበኛ የመንግስት ስራቸው የመመለስ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል ይላል - የተሻሻለው ረቂቅ ህግ፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በበኩሉ፤ ‹‹በምርጫ ቦርድ ተዘጋጅቶ የቀረበው የፓርቲዎችና የምርጫ ረቂቅ ሕግ እንከን የለሽ ነው፤ ፓርቲዎችንም በአግባቡ የሚያስተዳድር ነው›› በማለት ድጋፍ ሰጥቷል፡፡

Read 4615 times