Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 09:48

የአውሮፓ ዋንጫ ዘረኝነት እንዳጠላበት ተጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ፖላንድ ከግሪክ እንዲሁም ራሽያ ከቼክ ባደረጉት ጨዋታ የተጀመረ ሲሆን ውድድሩ በዘረኝነት ተግባራት ሊደፈርስ ይችላል የሚለው ስጋት አልበረደም፡፡
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በአውሮፓ ዋንጫው በሚያጋጥሙ ከዘረኝነት የተያያዙ ጥፋቶች ጥብቅ እርምጃ ሊወሰድ መዘጋጀቱን ሰሞኑን ሲያስታውቅ በፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ዘመቻ የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡  ከሳምንት በፊት በጨዋታ ላይ ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ማናቸውም ተግባራት ከተፈፀመ ሜዳ ለቅቄ እወጣለሁ በሚል የተናገረው የጣሊያኑ ማርዮ ባላቶሊ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚሸል ፕላቲኒ  ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በአውሮፓ ዋንጫው ማንም ተጨዋች ዳኛ ሳይፈቅድ ሜዳ ለቅቆ መውጣት አይቻልም ያለው ፕላቲኒ ይህን ህግ በመተላለፍ  በጨዋታ ላይ ሜዳ ለቅቆ የሚወጣ ተጨዋች በቢጫ ካርድ ይቀጣል ብሏል ፡፡ በጨዋታዎች ወቅት የዘረኝነት ጥፋት የሚፈጽሙ ብሔራዊ ቡድኖችም ከውድድሩ እስከመታገድ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችልም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አሳስቧል፡፡
14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የተለየ ገፅታ ሊኖረው እንደሚችልም እየተገለፀ ነው፡፡ በውድድሩ ከሚካፈሉት 16 ብሔራዊ ቡድኖች በተለይ ግሪክ፣ ስፔን፣ አየርላንድና ፖርቱጋል በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በመንገታገት ላይ መሆናቸው በሚኖራቸው ውጤታማነት ትኩረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
በአውሮፓ ዋንጫው ሻምፒዮናነታችን ብናስጠብቅ ለስፔን ችግሮች ፋይዳው እምብዛም ነው ያሉት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቪንሰንቴ ዴል ቦስኬ ሲሆኑ ይህ አስተያየታቸውን የተናገሩት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ብሔራዊ ቡድን ለማበረታታት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነበር፡፡ የ32 ዓመቱ የስፔን አምበል ዣቪ ኧርናንዴዝ በበኩሉ ብሔራዊ ቡድናችን ጥሩ ተጫውቶ ዋንጫውን ማሸነፍ ከቻለ ለህዝባችን መልካም ስሜት ይፈጥራል ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል፡፡ የ55 ዓመቱ የጣሊያን አሰልጣኝ ሴዛር ፔራንድሊ በበኩላቸው የአውሮፓ ዋንጫው ብሔራዊ ቡድኑንና የጣሊያን ህዝብ ለማቀራረብ  ሚና አለው ብለው ሲናገሩ በውድድሩ የምናስመዘግበው ውጤት ወሳኝነት የሚናቅ አይደለም ብለዋል፡፡ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን የአውሮፓ  ዋንጫ ተሳትፎው በአገሪቱ እግር ኳስ በተነሳው የጨዋታ ቅየራ ቁማር መወሳሰቡ ሲገለፅ እኝህ አሰልጣኝ አስፈላጊ ከሆነ ውድድሩን ላንሳተፍ እንችላለን ብለው ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን ፔራንድሊ በአውሮፓ ዋንጫው ስንሳተፍ በአገሪቱ እግር ኳስ ላይ የተነሱ ውዝግቦችን የሚያረግብ ውጤታማነት እንዲኖረን በመፈለግ ነው ብለዋል፡፡ ከአውሮፓ አገራት በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በመዘፈቅ ቀዳሚ በሆነችው ግሪክ በውድድሩ በሚኖራት ተሳትፎ ለአገሪቱ ህዝብ የደስታ እፎይታን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው ተጨዋቾቿ እየገለፁ ናቸው፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ፈርናንዶ ሳንቶስ ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት ስኬታማ ለመሆን ደም እንሰጣለን ብሎ ሲናገር  ወገኖቻችን ይተማመኑብን የሚል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
የአውሮፓ አገራት በኢኮኖሚ ቀውስ በተዳከሙበት  ሁኔታ የተጀመረው 14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ  በገቢ አቅሙ ግን ከዓለም ዋንጫ ተፎካካሪ እየሆነ ነው፡፡ የአውሮፓ ዋንጫው 1.3 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ ያስገኛል ተብሏል፡፡ በየጨዋታው በአማካይ 150 ሚሊዮን የቲቪ ተመልካች እንደሚኖረው ሲገመት በአንድ ጨዋታ አማካይ ገቢው 40.8 ሚሊዮን ዩሮ ተተምኗል፡፡ በሌላ በኩል በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ብሔራዊ ቡድኖች በየአገሮቻቸው የእግር ኳስ ፌደሬሽኖች በሚኖራቸው ስኬታማነት እንደሚሰጣቸው ቃል በተገባላቸው የቦነስ ክፍያዎች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ቀውስ እያሳጣ ነው፡፡ ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ በሚኖራቸው ስኬት በየአገራቸው ፌደሬሽኖች ለሚሰጣቸው የቦነስ ክፍያን መደራደራቸው ተጨዋቾችን ከአገር ፍቅር ስሜታቸው መቀዛቀዝ ጋር የሚያስተቻቸው ሆኗል፡፡
ከዩሮ 2012 አዘጋጅ አገራት አንዷ የሆነችው ዩክሬን እግር ኳስ ፌደሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ የዋንጫ ድል እስከ 13 ሚሊዮን ዩሮ ቦነስ  ማዘጋጀቱ ከፍተኛው ሽልማት ሰጭ አድርጎታል፡፡ የዩክሬን እግር ኳስ ፌደሬሽን  በዋንጫው ድል ለብሄራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች  በነፍስ ወከፍ ለመክፈል ያቀረበው ቦነስ 500ሺ ዩሮ ሲሆን ለዴንማርክ 404ሺ ዩሮ፤ ለጀርመን 300ሺ ዩሮ፤ ለፈረንሳይ 320ሺ ዩሮ በነፍስ ወከፍ ለየብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ቦነስ ለመክፈል የየአገራቱ ፌዴሬሽኖች ቃል ገብተዋል፡፡ የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌደሬሽን በበኩሉ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የ14ኛው አውሮፓ ዋንጫን ማሸነፍ ከቻሉ ለአያንዳንዳቸው 125ሺ ዩሮ በቦነስ ክፍያ ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች አገራቸው ለመወከል በአውሮፓ ዋንጫው ሲሳተፉ ለውጤታማነታቸው የቦነስ ክፍያ እንዲቀርብላቸው መደራደራቸው ለትችት ቢያጋልጣቸውም ይገባናል በሚል መከራከራቸውን  የአገሪቱ ጋዜጦች እየዘገቡ ናቸው፡፡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በ2008 እ.ኤ.አ በተደረጉ የአውሮፓ ዋንጫና በ2010 እ.ኤ.አ ለይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ከምድብ ማጣሪያ ማለፍ ያልቻለው በቦነስ ክፍያዎች አለመመቸት መሆኑ ከምክንያቶቹ መካከል ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡በእግር ኳስ የማበረታቻ ሽልማት ተጨዋቾች መፈለጋቸው ተገቢ መሆኑን የሚገልፁት የፈረንሳይ ተጨዋቾች  በፕሮፌሽናል ደረጃ የሚገባንን ጠየቅን እንጅ ባንክ እየሰበርን አይደለም ብለው የሚቀርብባቸውን ትችት ተከላክለዋል፡፡
የዩክሬን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቦነስ ክስያውን ከምድብ ማጣርያ ጀምሮ ለመክፈል ቢወስንም የፈረንሳይ፤ የጀርመንና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች ከየፌዴሬሽኖቸው ቃል የተገባላቸው የቦነስ ከፍያ ተግባራዊ የሚሆነው ቡድኖቹ የምድብ ማጣርያውን አልፈው ጥሎ ማለፍ ከገቡ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
የሚጠበቁ የምድብ ጨዋታዎች
ዛሬ ከምድብ 2 በጀርመን ከፖርቱጋል
ነገ ከምድብ 3 ስፔን ከጣሊያን
ሰኞ ከምድብ 4  ፈረንሳይ ከእንግሊዝ
ረቡእ ከምድብ 2 ሆላንድ ከጀርመን

14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ፖላንድ ከግሪክ እንዲሁም ራሽያ ከቼክ ባደረጉት ጨዋታ የተጀመረ ሲሆን ውድድሩ በዘረኝነት ተግባራት ሊደፈርስ ይችላል የሚለው ስጋት አልበረደም፡፡የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በአውሮፓ ዋንጫው በሚያጋጥሙ ከዘረኝነት የተያያዙ ጥፋቶች ጥብቅ እርምጃ ሊወሰድ መዘጋጀቱን ሰሞኑን ሲያስታውቅ በፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴ ዘመቻ የሚያደርጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ድጋፍ አግኝቷል፡፡  ከሳምንት በፊት በጨዋታ ላይ ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ማናቸውም ተግባራት ከተፈፀመ ሜዳ ለቅቄ እወጣለሁ በሚል የተናገረው የጣሊያኑ ማርዮ ባላቶሊ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚሸል ፕላቲኒ  ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በአውሮፓ ዋንጫው ማንም ተጨዋች ዳኛ ሳይፈቅድ ሜዳ ለቅቆ መውጣት አይቻልም ያለው ፕላቲኒ ይህን ህግ በመተላለፍ  በጨዋታ ላይ ሜዳ ለቅቆ የሚወጣ ተጨዋች በቢጫ ካርድ ይቀጣል ብሏል ፡፡ በጨዋታዎች ወቅት የዘረኝነት ጥፋት የሚፈጽሙ ብሔራዊ ቡድኖችም ከውድድሩ እስከመታገድ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችልም የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አሳስቧል፡፡

14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ በአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የተለየ ገፅታ ሊኖረው እንደሚችልም እየተገለፀ ነው፡፡ በውድድሩ ከሚካፈሉት 16 ብሔራዊ ቡድኖች በተለይ ግሪክ፣ ስፔን፣ አየርላንድና ፖርቱጋል በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በመንገታገት ላይ መሆናቸው በሚኖራቸው ውጤታማነት ትኩረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡

በአውሮፓ ዋንጫው ሻምፒዮናነታችን ብናስጠብቅ ለስፔን ችግሮች ፋይዳው እምብዛም ነው ያሉት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቪንሰንቴ ዴል ቦስኬ ሲሆኑ ይህ አስተያየታቸውን የተናገሩት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ብሔራዊ ቡድን ለማበረታታት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነበር፡፡ የ32 ዓመቱ የስፔን አምበል ዣቪ ኧርናንዴዝ በበኩሉ ብሔራዊ ቡድናችን ጥሩ ተጫውቶ ዋንጫውን ማሸነፍ ከቻለ ለህዝባችን መልካም ስሜት ይፈጥራል ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል፡፡ የ55 ዓመቱ የጣሊያን አሰልጣኝ ሴዛር ፔራንድሊ በበኩላቸው የአውሮፓ ዋንጫው ብሔራዊ ቡድኑንና የጣሊያን ህዝብ ለማቀራረብ  ሚና አለው ብለው ሲናገሩ በውድድሩ የምናስመዘግበው ውጤት ወሳኝነት የሚናቅ አይደለም ብለዋል፡፡ የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን የአውሮፓ  ዋንጫ ተሳትፎው በአገሪቱ እግር ኳስ በተነሳው የጨዋታ ቅየራ ቁማር መወሳሰቡ ሲገለፅ እኝህ አሰልጣኝ አስፈላጊ ከሆነ ውድድሩን ላንሳተፍ እንችላለን ብለው ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን ፔራንድሊ በአውሮፓ ዋንጫው ስንሳተፍ በአገሪቱ እግር ኳስ ላይ የተነሱ ውዝግቦችን የሚያረግብ ውጤታማነት እንዲኖረን በመፈለግ ነው ብለዋል፡፡ ከአውሮፓ አገራት በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በመዘፈቅ ቀዳሚ በሆነችው ግሪክ በውድድሩ በሚኖራት ተሳትፎ ለአገሪቱ ህዝብ የደስታ እፎይታን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው ተጨዋቾቿ እየገለፁ ናቸው፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ፈርናንዶ ሳንቶስ ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት ስኬታማ ለመሆን ደም እንሰጣለን ብሎ ሲናገር  ወገኖቻችን ይተማመኑብን የሚል መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

የአውሮፓ አገራት በኢኮኖሚ ቀውስ በተዳከሙበት  ሁኔታ የተጀመረው 14ኛው የአውሮፓ ዋንጫ  በገቢ አቅሙ ግን ከዓለም ዋንጫ ተፎካካሪ እየሆነ ነው፡፡ የአውሮፓ ዋንጫው 1.3 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ ያስገኛል ተብሏል፡፡ በየጨዋታው በአማካይ 150 ሚሊዮን የቲቪ ተመልካች እንደሚኖረው ሲገመት በአንድ ጨዋታ አማካይ ገቢው 40.8 ሚሊዮን ዩሮ ተተምኗል፡፡ በሌላ በኩል በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ብሔራዊ ቡድኖች በየአገሮቻቸው የእግር ኳስ ፌደሬሽኖች በሚኖራቸው ስኬታማነት እንደሚሰጣቸው ቃል በተገባላቸው የቦነስ ክፍያዎች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ቀውስ እያሳጣ ነው፡፡ ብሔራዊ ቡድኖች በውድድሩ በሚኖራቸው ስኬት በየአገራቸው ፌደሬሽኖች ለሚሰጣቸው የቦነስ ክፍያን መደራደራቸው ተጨዋቾችን ከአገር ፍቅር ስሜታቸው መቀዛቀዝ ጋር የሚያስተቻቸው ሆኗል፡፡

ከዩሮ 2012 አዘጋጅ አገራት አንዷ የሆነችው ዩክሬን እግር ኳስ ፌደሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ የዋንጫ ድል እስከ 13 ሚሊዮን ዩሮ ቦነስ  ማዘጋጀቱ ከፍተኛው ሽልማት ሰጭ አድርጎታል፡፡ የዩክሬን እግር ኳስ ፌደሬሽን  በዋንጫው ድል ለብሄራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች  በነፍስ ወከፍ ለመክፈል ያቀረበው ቦነስ 500ሺ ዩሮ ሲሆን ለዴንማርክ 404ሺ ዩሮ፤ ለጀርመን 300ሺ ዩሮ፤ ለፈረንሳይ 320ሺ ዩሮ በነፍስ ወከፍ ለየብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ቦነስ ለመክፈል የየአገራቱ ፌዴሬሽኖች ቃል ገብተዋል፡፡ የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌደሬሽን በበኩሉ የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የ14ኛው አውሮፓ ዋንጫን ማሸነፍ ከቻሉ ለአያንዳንዳቸው 125ሺ ዩሮ በቦነስ ክፍያ ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች አገራቸው ለመወከል በአውሮፓ ዋንጫው ሲሳተፉ ለውጤታማነታቸው የቦነስ ክፍያ እንዲቀርብላቸው መደራደራቸው ለትችት ቢያጋልጣቸውም ይገባናል በሚል መከራከራቸውን  የአገሪቱ ጋዜጦች እየዘገቡ ናቸው፡፡ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በ2008 እ.ኤ.አ በተደረጉ የአውሮፓ ዋንጫና በ2010 እ.ኤ.አ ለይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ከምድብ ማጣሪያ ማለፍ ያልቻለው በቦነስ ክፍያዎች አለመመቸት መሆኑ ከምክንያቶቹ መካከል ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡በእግር ኳስ የማበረታቻ ሽልማት ተጨዋቾች መፈለጋቸው ተገቢ መሆኑን የሚገልፁት የፈረንሳይ ተጨዋቾች  በፕሮፌሽናል ደረጃ የሚገባንን ጠየቅን እንጅ ባንክ እየሰበርን አይደለም ብለው የሚቀርብባቸውን ትችት ተከላክለዋል፡፡

የዩክሬን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቦነስ ክስያውን ከምድብ ማጣርያ ጀምሮ ለመክፈል ቢወስንም የፈረንሳይ፤ የጀርመንና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች ከየፌዴሬሽኖቸው ቃል የተገባላቸው የቦነስ ከፍያ ተግባራዊ የሚሆነው ቡድኖቹ የምድብ ማጣርያውን አልፈው ጥሎ ማለፍ ከገቡ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

የሚጠበቁ የምድብ ጨዋታዎች

ዛሬ ከምድብ 2 በጀርመን ከፖርቱጋል

ነገ ከምድብ 3 ስፔን ከጣሊያን

ሰኞ ከምድብ 4  ፈረንሳይ ከእንግሊዝ

ረቡእ ከምድብ 2 ሆላንድ ከጀርመን

Read 2033 times