Monday, 15 July 2019 10:23

“የይሁዳ ገመድ” የግጥም መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በጅማ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የህክምና ተማሪ በሆነው ወጣት ገጣሚ በዛብህ ብርሃኑ የተፃፉ ግጥሞችን ያካተተው “የይሁዳ ገመድ” የግጥም መድብል በገበያ ላይ ዋለ፡፡
መጽሐፉ በፍቅር፣ በፍልስፍና በማህበራዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከ40 በላይ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን፤  ጅማ ዶሎሎ ሆቴል ገጣሚው በሰጠው አስተያየቶች፤  “የሜዲሲን ትምህርት ከፍተኛ ጊዜና ጥሞና የሚፈልግ ቢሆንም ለስነ ጽሑፍ ባለኝ ፍቅር የተነሳ ከጥናት ጊዜዬ እየቆጠብኩ የሚሰማኝን ስሜት ወደ ግጥም እየቀየርኩ ካጠራቀምኩ በኋላ ሊታተም ችሏል ብሏል፡፡
ከልጅነቱ ጀምሮ በተወለደበት ሃዋሳ በተለያዩ የኪነ ጥበብ ክበቦች ሲሳተፍ እንደነበረ የገለፀው በዛብህ፤ አሁንም ተጽፈው ያለቁ ሁለት ረጅም ልብወለዶች እንዳሉት ገልፆ፤ ሁኔታዎች ሲመቻቹ የህትመት ብርሃን እንደሚያዩ ተናግሯል፡፡ “የይሁዳ ገመድ” የግጥም መድበል በ77 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ48 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4871 times