Saturday, 06 July 2019 14:38

የግጥም ጥግ

Written by  ዘላለም ገበየሁ
Rate this item
(6 votes)

 አስመሳይነት

እግዜር ደብረነው ብቻውን ለመደ
ክፋታችን ገፍቶት ጥሎን ተሰደደ፤
ግዕዝ ከሚናገር ተንኮለኛ ሰይጣን
ጋብቻ ፈጽመን ሰው ልንገድል ወጣን
ለአክ-ቲቪ - ስቶቻችን
አዳም በጥፋቱ ቡትቶም አጣና ገላው ርቃን ቀረ
ወፍና አራዊቱ በአዳም ብልት ሣቁ አዳምም
አፈረ፣
እኔን የገረመኝ የአራዊቱ ደስታ
እርቃን ብልት ይዘው በአዳም ላይ ጨዋታ
በገሃነም ስር መጽደቅ
(ዘላለም ገበየሁ)


Read 3125 times