Saturday, 22 June 2019 11:23

ሲትረስ ሲትረስ ኢንተርናሽናል 800 ሺህ ብር ግምት ያለው አንድ ሚሊዮን አኳ ታብስ በነፃ ሰጠ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)


               የውሃ ማከሚያ እንክብል አኳታብስ አስመጪ የሆነው ሲትረስ ኢንተርናሽናል በኮሌራ ለተጠቁ አካባቢዎች 800ሺህ ብር ግምት ያለው አንድ ሚሊዮን አኳታብስ የውሃ ማከሚያ እንክብሎች በነፃ ሰጠ፡፡
ባለፈው ረቡዕ በስካይ ላይት ሆቴል የተካሄደው የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ስምፖዚየም ሲያበቃ የሲትረስ ኢንተርናሽናል ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ምናሴ ክፍሌ መድኃኒቶቹን ሲያስረክቡ፣ የኮሌራ አጣዳፊ ወረርሽኝ በአገሪቱ ተከስቶ ሕዝብ ሲፈጅ ዝም ማለት ስለማንችል የድርሻችንን ለመወጣት ይህን ስጦታ አድርገናል ብለዋል፡፡
አቶ ምናሴ ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልል ከተፈናቀሉ ወገኖች ጋር ተያይዞ በተከሰተው የአተት ወረርሽኝ በሽታ 30 ሚሊዮን ሊትር ውሃ ማከም የሚያስችል 1.5 ሚሊዮን ውሃ ማከሚያ አኳታብስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ዘንድሮም 20 ሚሊዮን  ሊትር ውሃ ማከም የሚያስችል ለአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ሱማሌ፣ አዲስ አበባና በሌሎችም ክልሎች የተሰራጨውን ኮሌራ በማከም ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመውጣት ይህን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው መድኀኒቱን ለማስመጣት የውጭ ምንዛሪ ከየት ታመጣላችሁ ተብለው ሲመልሱ “የውጭ ምንዛሪ እጥረት አለ፤ የምናስመጣው አኳታብስ ከመድኃኒት ስለሚመደብ  መንግሥትም ቅድሚያ በመስጠት ይደግፈናል” ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኮሌራ ወረርሽኝ እየተጠቁ ላሉ አካባቢዎች አስቸኳይ የአኳታብስ ውሃ ማከሚያ እንክብል ድጋፍ ለማድረግ በጠየቅነው መሠረት የፌደራል የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ፈቅዶልን በዛሬው እለት ይህንን መድኃኒት አስረክበናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡  

Read 1956 times