Saturday, 22 June 2019 11:08

ኮሚሽኑ የቀድሞ አርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊትን ሊያቋቁም ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

የሠራዊቱ አባላት ከ5 ሺህ በላይ ይሆናሉ

             የቀድሞ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሠራዊት አባላትን የፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለማቋቋም ቃል መግባቱን ሠራዊቱን መልሶ የማቋቋም አስተባባሪ ወ/ሮ እማዋይሽ ዘውዱ ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡
ሠራዊቱን መልሶ የማቋቋም ኮሚቴው በጉዳዩ ላይ ከአደጋ መከላከልና ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር መወያየቱን የገለፁት ወ/ሮ እማዋይሽ፤ መንግስት ተጣርቶ የቀረበለትን የሰው ሃይል መልሶ ለማቋቋም ቃል ገብቷል ብለዋል፡፡
በአሁን ወቅት በየቦታው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ተሳትፎና ማንነት የተመለከቱ መረጃዎችን ኮሚቴው እያጣራ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ እማዋይሽ፤ በአጠቃላይ መደራጀትና መቋቋም የሚያስፈልጋቸው የሠራዊቱ አባላት ከ5ሺህ በላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሠራዊት አባላቱ በአራት ምድብ የሚከፈሉ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪዋ፤ በመንግስት ታስረው የነበሩ፣ ከኤርትራ የመጡ፣ በዘመቻ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በዘመቻ ወቅት አባታቸውን ያጡ ልጆች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ባህር ዳር ላይ 1900 (አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ ያህል) የሠራዊቱ አባላት ለመቋቋም ተመዝግበው ይገኛሉ ያሉት አስተባባሪዋ፤ በቀጣይ አባላቱ በፈለጉት የስራ መስክ እንዲሠማሩ መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዶ ለማቋቋም ቃል መግባቱን አስታውቀዋል፡፡

Read 11555 times