Saturday, 02 June 2012 10:45

“የጐርደነ ሴረ” መጽሐፍ ነገ ፤“ምስጢር” ረቡዕ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሃጂ አብዱልፈታህ አብዱላህ የተዘጋጀው የጐርደነ ሴረ (የወለኔ ሕዝብ የባህል ሕግ) መጽሐፍ ነገ በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ትልቁ አዳራሽ እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ ከጧቱ 3 ሰዓት የሚመረቀውን መጽሃፍ አስመልክቶ ደራሲና አዘጋጁ ሃጂ አብዱልፈታህ ለዝግጅት ክፍላችን ሲናገሩ “የባህል ፍትህ ሥርአታችንን አስመልክቶ ያለን ሀገራዊ እውቀት አናሳነት ክፍተትን ለመሙላት የተዘጋጀ ነው” ብለዋል፡፡ 160 ገጽ ያለው መጽሐፉ በ29 ብር ለንባብ ቀርቧል፡፡ በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር “ምስጢር” የተሰኘ መፅሐፍ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ በመጪው ረቡዕ ከቀኑ 10 ሰዓት በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃሕፍት ኤጀንሲ የሚመረቀውን መፅሐፍ ያዘጋጁት የማህበሩ አባል ፀሐይ ይሰማው ናቸው፡፡

 

 

Read 820 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 10:47