“ሜን ኢን ብላክ 3” የተሰራው በሶኒ ፒክቸርስ ሲሆን የፊልም ኩባንያው በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሌሎች ትላልቅ ፊልሞችን ለገበያ በማብቃት ገበያውን የመቆጣጠር እቅድ እንዳለው ሮይተርስ አመልክቷል፡፡ “ሜን ኢን ብላክ 3” እንዲሁም በድጋሚ የተሰሩት “ዘ አሜዚንግ ስፓይደር ማን” እና “ቶታል ሪኮል” ፊልሞችን ለማስተዋወቅ 1ቢሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉ ተዘግቡዋል፡፡
በሶኒ ፒክቸርስ በ215 ሚሊዮን ዶላር በጀት በድጋሚ የተሰራው “ዘ አሜዚንግ ስፓይደር ማን” ለወጪ ቅነሳ ሲባል አዲስ ተዋናይ እንዲሰራው መደረጉን የገለፀው ሮይተርስ፤ ከ12 ዓመታት በፊት በሸዋዚንገር ተተውኖ የነበረው “ቶታል ሪኮል” በኮሊን ፋሬል እንደተሰራና 125 ሚሊዮን ዶላር ወጭ እንደተደረገበት አውስቷል፡፡