Saturday, 18 May 2019 00:00

“የይሁዳ መዳፎች” ልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በደራሲ አንድሪያስ ይዘንጋው የተደረሰውና በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደረገው “የይሁዳ መዳፎች” የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሰርቆ በወጣ መረጃ ምክንያት የደረሰውን ጥፋት የሚያሳየው ልቦለዱ፤ ፖለቲከኞች እታገልለታለሁ ከሚሉት ህዝብና ሀገር ርቀው በራሳቸው ምናብ በተፈጠረ ዓለም ውስጥ እንዴት እንደሚዳክሩ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚያነጽር ታሪክ መሆኑን ደራሲው በመግቢያቸው ጠቁመዋል፡፡ በ172 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ95 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6141 times