Saturday, 23 March 2019 14:24

የ“ጉዞ አድዋ” 6 የሞባይል ፎቶ አውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


        55 ተጓዦች የተሳተፉበትና ከሀረር እስከ አድዋ 61 ቀናት የፈጀውን ጉዞ የሚያስታውስና ተጓዦች በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ለማስታወሻ ያስቀሯቸው ፎቶዎች አውደ ርዕይ ዛሬ አመሻሽ ላይ ይጠናቀቃል፡፡ ሐሙስ 11፡00 ላይ በብሔራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ የተከፈተው ይሄው አውደ ርዕይ፤ 61 ፎቶዎችን ያካተተ ሲሆን ተጓዦቹ ዛሬ አመሻሽ ላይ እንደሚዘጋም ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የ“ጉዞ አድዋ 6” የመዝጊያ ፕሮግራም ባለፈው ረቡዕ ምሽት በጣይቱ ሆቴል ግቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡
በእለቱ ከሽሬ የመጡ የጉዞ አድዋ አድናቂዎችን ጨምሮ የሀረር ተጓዦችና የአዲስ አበባዎቹም የተገኙ ሲሆን በተጓዦች ግጥም፣ በሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ዲስኩር ፉከራና ሽለላ እንዲሁም ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በዜማ ነጋሪት ባንድ ታጅበው ቀርበዋል፡፡ የዘንድሮው “ጉዞ አድዋ” 55 ተጓዟችን ያሳተፈ ሲሆን 4ቱ ከሀረር፣ 44ቱ ከአዲስ አበባ፣ 5ቱ ከመቀሌና በቀን 42 ኪ.ሜ እየሮጡ የተጓዙ ሁለት ሯጮችን ከአዲስ አበባ ያቀፈ ነው፡፡

Read 6028 times