Saturday, 26 May 2012 13:02

የቼዝ ምድር ለንባብ በቃ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በአብዱልበር ነስሮ የተፃፉ ግጥሞች እና አጫጭር ልቦለዶች የተካተቱበት “የቼዝ ምድር” መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ አስር ገፅ የእጅ ፅሁፍ ስካን ተደርጐ የተካተተበት መፅሐፍ 76 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 25 ብር ነው፡፡ ሰላሳ ግጥሞች እና ሦስት ልቦለዶች የያዘው መፅሐፍ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እየተሸጠ ነው፡፡በሌላም በኩል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ጤርጥዮስ ከቫቲካን በሚል የብዕር ስም በሚፅፋቸው መጣጥፎቹ የሚታወቀው ሽመልስ ይፍሩ “የአማኝ አሳማኝ እሰጥ አገባ” የሚል መፅሐፍ አዘጋጅቶ ለንባብ አቀረበ፡፡ 200 ገፆች ያሉት መፅሐፍ በ30 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ መፅሐፉ ነገ ከሰዓት በመካኒሳው የመካነ ኢየሱስ ኮሌጅ ይመረቃል፡፡

Read 919 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 13:04