Saturday, 26 May 2012 12:54

የደጃዝማች በላይ ዘለቀ 100ኛ ዓመት ተከበረ የቅዱስ የሬድ 1500ኛ ዓመት ሳምንት ተከበረ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

የታላቁ አርበኛ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ 100ኛ ዓመት ልደት ከትናንት ወዲያ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ልዑል ራስ መኮንን አዳራሽ ተከበረ፡፡ ከቀኑ ሰባት ሰዓት የተጀመረው ዝግጅት ያሰናዱት የጀግናው አርበኛ ቤተሰቦች እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ተቋም በህብረት ነው፡፡ በዝግጅቱ ጥናታዊ ፅሁፍ፣ በአርቲስት ጌትነት እንየው “የበላይ መጨረሻ’ የሚል መነባንብ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር ተማሪዎች ‘አባ ኮስትር’ የሚል ቅንጭብ ትያትር ያቀረቡ ሲሆን አርቲስት አሰለፈች አሽኔ፣ አርቲስት አሸብር በላይ እና አርቲስት ገነት ማስረሻ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ የዜማ አባት የሚባለው ቅዱስ ያሬድ የተወለደበት 1500ኛ ዓመት ባለፈው ቅዳሜ በአክሱም ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ፡፡ በዝግጅቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ተገኝተዋል፡፡ በዚሁ ወቅትም የቅዱስ ያሬድን ብቻ ሳይሆን የዘጠኙ ቅዱሳንንና የንግሥት ሳባ መንግሥትን 3ሺህኛ ዓመት መዘከር አለብን ብለዋል፡፡በአከባበሩ 50 ሊቃውንት ከጐንደር እንዲሁም ከሌሎች ቦታዎች የተለያዩ አክሱም በመሄድ ያሬዳዊ ዜማዎች አሰምተዋል፡፡

 

 

Read 3212 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:57