Saturday, 26 May 2012 12:49

“የመጨረሻዋ ቀሚስ” ፊልም በስምንት ቋንቋዎች ይተረጐማል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት እሁድ ቦሌ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ለሃምሳ እንግዶች ታይቶ የተመረቀው “የመጨረሻዋ ቀሚስ” ፊልም በስምንት ቋንቋዎች እንደሚተረጐም አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የ2001 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ ሴቶችን ሲያወያዩ ብርሃኔ ከልካይ የተባሉ ተሳታፊ በጠየቁት ጥያቄ መነሻ ሀሳቡን የቀዳው ፊልም ባለቤቶች ፊልሙን በሀገር ውስጥ 33 ሺህ አባላት ላሉት የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር አበርክተዋል፡፡የኤችአይቪ/ኤድስ እና ሴቶች ጉዳዩን በማነሳሳት በአማርኛ የተሰራው ፊልሙ ወደ ኦሮምኛ፣ ትግሪኛ፣ አፋርኛ፣ ጉራጊኛ፣ ጋሞኛ፣ አገውኛ እና ሶማሊኛ ቋንቋዎች ይተረጐማል፡፡

በ”ስላንቺ” እና “ላውንደሪ ቦይ” ፊልሞቹ የሚታወቀው ሀኖስ ፊልም ፕሮዳክሽን ያቀረበውን የ108 ደቂቃ ፊልም፤ በልዑል ሰሎሞን እና ፀጋዬ ዮሐንስ ፅፈውት ልዑል ሰለሞን አዘጋጅቶታል፡፡ በፊልሙ ማህሌት ሹመቴ፣ ፈለቀ አበበ፣ አዜብ ወርቁ፣ ሰብለ ወርቁ እና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

 

 

 

 

Read 1599 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:52