Saturday, 26 May 2012 12:38

ዶና ሰመር ከሞቷ በኋላ በገበያው አንሰራራች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት በ63 ዓመቷ በካንሰር ህመም ህይወቷ ያለፈው  ዶና ሰመር ከሞተች በኋላ በሳምንት ውስጥ እስከ 50ሺ የአልበሞቿን ቅጂዎች በመሸጥ በገበያው ማንሰራራቷን ቢልቦርድ አስታወቀ፡፡ በ1970ዎቹ እና 80 ዎቹ የዲስኮ  ንግስት ለመባል የበቃችው እና የሴት ሙዚቀኞች ፈርቀዳጅነቷ የሚወሳላት ዶና በሙያው በቆይችባቸው 43 ዓመታት 17 አልበሞችን በመስራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዝና እና ክብር ያገኘች ናት፡፡  በዶና ሰመር  ሞት ሃዘናቸውን ከገለፁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ግንባር ቀደም ሲሆኑ በድምፃዊዋ ሞት ቤተሰባቸውን ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማው በገለፁበት መግለጫ ዶና ድምጿ ሊረሳ የማይችልና ቶሎ ያጣናት እውነተኛ የዲስኮ ንግስት ነበርች ብለው አወድሰዋል፡፡ በአር ኤንድ ቢ፤በፖፕ፤ በዲስኮ፤ በሮክ፤ በዳንስና በጎስፔል ሙዚቀኛነቷ ዶና ሰመር ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ከበቁ አርቲስቶች ተርታ የምትጠቀስ ነበረች፡፡

ሰሞኑን የዶና ሰመር ተወዳጅ ዜማዎች ላቭ ቱ ላቭ ዩ ቤቢ፤ ባድ ገርልስ፤ሆት ስታፍ፤ ላስ ዳንስና ሺ ዎርክስ ሃርድ ፎር ዘ መኒ የተባሉት በመላው ዓለም ተፈላጊነታቸው መጨመሩን ያወሳው ቢልቦርድ መፅሄት ከሳምንት በፊት የተካሄደው የ2012 ቢልቦርድ አዋርድ መታሰቢያነቱ ለእሷ ሆኖ በከፍተኛ ክብር ስንብት እንደተደረገላት ጨምሮ አውስቷል፡፡

 

 

Read 1167 times Last modified on Saturday, 26 May 2012 12:42