Monday, 11 February 2019 00:00

“የሚመጣው መከራና ፍርድ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በተክለ ኪዳን የተሰናዳውና “በመላው በዓለም ላይ ያለው የሰው ዘር በሙሉ መነሻቸው ኢትዮጵያ ናት በሚል ማጠንጠኛ የተዘጋጀው “የሚመጣው መከራና ፍርድ” ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በዋናነት ኢትዮጵያዊነት ከአዳምና ሄዋን ጀምሮ የነበረና ከእግዚአብሔር የተሰጠ መሆኑን የሚያትት ሲሆን ከእግዚአብሔር የሆነውን እውነት፣ እውቀት፣ ምስጢረትና ትንቢቶችን ለትውልድ በስፋት ለማስተዋወቅ መሰናዳቱን ፀሐፊው በመግቢያቸው አስፍረዋል፡፡
በ340 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ125 ብር ለገበያ ቀርቧል በመፅሐፉ ላይ መወያየት ለሚፈልግ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ እንደሆኑ አስታውቀዋል፡፡

Read 4920 times