Saturday, 12 January 2019 14:21

የአባቶች ሲጋራ አጫሽነት… ልጅ ላለመውለድ ምክንያት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ትዳር የሁለት ተጋቢዎችን መተማመን በጣም የሚፈልግ መሆኑን የተረዳሁት እኔና ባለቤቴ ለፍቺ በሂደት ላይ በነበርንበት ወቅት ነው፡፡ እኔና ባለቤቴ በተጋባን በስምንት አመታችን ስንጉዋጉዋለት የነበረ ነገር ግን የተረሳ ነገር ተከሰተ፡፡ ይኼውም ልጅ ለመውለድ ብዙ ሞክረን ስላቃተን ከዚህ በሁዋላ ስለልጅ ማሰብ የለብንም ብለን ተማምለን ትተነው ሳለ ነገር ግን በስምንት አመታችን እርግዝና ተከሰተ፡፡ ጊዜውን ጠብቆም ልጁ ተወለደ። እኔ ሳላውቀው ባለቤቴ ለካስ ጥርጣሬ ላይ ነበር። ይህ ልጅ እውነት የኔ ነው? ወይንስ? በሚል፡፡ እኔ ወልጄ እንደተኛሁ ከዚያው ከሆስፒታል ናሙና እንዲሰጠው በመጠየቅ የDNA ምርመራውን ወደ ኬንያ በመላክ ውጤት ይጠባበቃል ፡፡ እኔ ስለጉዳዩ ምንም ሳላውቅ እርሱ ውጤቱን ተቀብሎ ልጁ መሆኑን አረጋግጦ ኑሮአችንን ቀጠልን፡፡ የሁዋላ ሁዋላ ግን ወሬውን ስሰማ በጣም ተበ ሳጨሁ፡፡ እኔን ለምን አላማከርከኝም? ለምንስ ፈቃዴን አልጠየቅህም? ብለውም …በቃ ተጠራ ጥሬ ነው…አለኝ። ስለዚህ እኔ በአንተ ላይ ሌላ ሰው ደርቤ እንዳረገዝኩ ካሰብክ በመካ ከላችን መተማመን ስለሌለ ኑሮው በቃኝ ብዬ ትዳሬን አፈረስኩ፡፡ በጊዜው የተፈጠረው ነገር እጅግ አሳዝኖኝ ነበር፡፡ ባልና ሚስት በመካከላቸው መተማመን ከሌለና በግልጽ መወያየት ካልቻሉ ኑሮ የይስሙላ ነው። እንደእኔ እምት የይስሙላ ኑሮ ከመኖር ደግሞ ቢቀር ይሻላል፡፡
እታገኝ ኃይሌ ከካዛንቺስ
ከላይ የተገለጸው ልጅ ሳንወልድ ቀረን በማለት ባልና ሚስቱ ተስፋ የቆረጡበት ምክንያት በአንዳንዶች ዘንድ አመታትን ቆጥሮ የሚሳካበት ሁኔታ እንደሚኖር የሚያሳይ እውነታ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ልጅ ያለመውለድ ችግር የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ተብሎ ይለያል፡፡ የረጅም ጊዜ ልጅ ያለማፍራት ችግር ማለት ለአመታት ያክል ሁለቱ ጥንዶች ልጅ መውለድ ሳይችሉ የሚቆ ዩበት ሁኔታ ነው። የአጭር ጊዜው ግን ምናልባትም ልጅ ከወለዱም በሁዋላ ምናልባት ከሚጠ ቀሙዋቸው መድሀኒቶች ወይንም የአኑዋኑዋር ሁኔታ የተነሳ ልጅ መውለድ ዘግየት ሲል የሚ ጠቀስ ነው እንደባለሙያዎች እማኝነት፡፡  
በአማካይ ወደ 15% የሚሆኑ ባለትዳሮች ልጅ መውለድ እንደሚፈልጉ እሙን ቢሆንም ከተገናኙ ወይንም ወሲብ መፈጸም ከጀመሩ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ልጅ መውለድ ሊያቅታቸው ይችላል፡፡ በእርግጥ የወሲብ ግንኙነታቸው ምንም መከላከያ ያልተደረገለት እና የወሲብ ግንኙነቱ በአስፈላጊው ጊዜ ሁሉ የተፈጸመ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ተጋቢዎች ልጅ መውለድ ሳይችሉ ከቀሩ በማህበራዊ እና በስነልቡና ባጠቃላይም በሚመሩት ሕይወታቸው ላይ ጫና ማሳደሩና በጋብቻቸው ላይም ሊያደርጉት የሚገባውን በጎ ነገር እን ዲቀንሱ የሚያስገድድበት ሁኔታ ይስተዋላል። ቁጥራቸው ወደ /1644/ በሚሆኑ ልጅ መውለድ ሳይችሉ በቀሩ ወንዶች ላይ የተደረገው አለም አቀፍ የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው፤
አንድ ወንድና አንዲት ሴት በጋብቻም ይሁን በጉዋደኝነት በሚገናኙበት ጊዜ አንዳንዶች ለአጭር አንዳንዶች ደግሞ ለረጅም ጊዜ ሌሎች እስከመጨረሻውም ልጅ መውለድ ሳይችሉ ሊቀሩ ይች ላሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያትም በብዙ ጥናቶች ተዳስ የተገኙት ውጤቶች የተለያዩ ናቸው፡፡
ወንዶች ሊኖራቸው የሚገባው የዘር ፈሳሽ (sperm) መጠን መቀነስ ወይንም መዳከም፤
እናቶች እርግዝና ሊከሰት በሚችልበት ጊዜ ሲጋራ የሚያጤሱ ከሆነ እና የሚገናኙት የዘርፍሬው ደካማ ከሆነ ሰው ጋር ከሆነ፤
እድሜ ከገፋ እና የሰውነት ክብደት ከፍተኛ ከሆነ ለረጅም ጊዜ ልጅ መውለድ አለመቻል ሊገጥም እንደሚችል ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡
በስዊድን ቁጥራቸው /104/ በሚሆኑ እድሜያቸው በ17-20 በሆኑት ወንዶች ላይ ተደርጎ በነበ ረው ጥናት እናቶች ኒኮቲን ለተባለው ንጥረ ነገር መጋለጣቸው እና በኑሮአቸው ያለው የኢኮ ኖሚ ግብአት እንዲሁም ወንድ ልጆች እራሳቸው አጫሽ ሲሆኑ በተጨማሪም ወንዶች ልጆች  አጫሽ ከሆኑ አባቶቻቸው በሚወርሱት ምክንያት የሚኖራቸው ልጅ ያለመውለድ ችግር ምንም ከማያጨሱት ወንዶች ወደ 41/% sperm ብቃት ማነስ እና 51/% የsperm መጠን መቀነስ ይገጥማቸዋል፡፡
በርካታ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እናት ሲጋራ የምታጤስ ከሆነ በማህጸንዋ ለሚኖረው ጽንስ አደገኛ ሲሆን በዚህ ጥናት ግን አባትየው የሚያጤስ ከሆነ የተረገዘው ልጅ sperm ቁጥር ሊቀንስ የሚችል መሆኑ በአዲስ መልክ የተገኘ የጥናት ውጤት ነው፡፡ በእርግጥ ይህ በቀጥታ ግንኙነቱ ምን እንደሆነ ለጊዜው ባይገለጽም የሚያጤሱ አባቶች በሚረገዘው ልጅ ላይ ተፈጥ ሮአዊ ችግር (malformations) እንዲከሰት የሚያስችል መሆኑ በተለያዩ መንገዶች የተጠቀሰ ሲሆን ልጅ መውለድ አለመቻል ከችግሮቹ እንደ አንዱ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ጆናታን አልሰን የተባሉ ምሁር ይገልጻሉ፡፡  
በአለም ዙሪያ ያሉ ባለሙያዎች ልጅ ባለመውለድ ዙሪያ ለመፍትሔው ያልተቋረጠ ጥናት በማድረግ ላይ ያሉ በመሆኑ ይህ ልጅ ያለመውለድ ችግር እና ሲጋራ አጫስነት እንዴት እንደ ሚገናኝ ለመመልከት ተሞክሮአል፡፡ በዚህም እናቶች በእርግዝና ጊዜ ሲጋራን የሚያጤሱ ከሆነ ለጽንሱ ምን ያህል ጎጂ እንደሚሆን ከግምት ውስጥ የገባ ሲሆን አባቶች ወይንም ባሎች የሚያ ጤሱ ከሆነ ደግሞ የወንድ ልጃቸው sperm ቁጥር ወይንም መጠን እንደሚቀንስ እርግጥ ሆኖ አል፡፡
በእርግጥ ሲጋራ ማጤስ በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ላይ የራሱን ተጽእኖ እንደሚያሳድር እና ገና ጽንሱ መፈጠር ሲጀምር በሚኖረው መተላለፍ ሳቢያ የወንዶችን የዘር ፍሬ ብቃት እና ጥራት ደረጃ ዝቅ እንደሚያደርገው የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኛው በድንገት የሚከሰተው ለውጥ የሚከሰተው ደግሞ ከአባቶች አጫሽነት ሲሆን በእርግጥ የወንዶች እድሜ እና የተለያዩ ሕመሞ ችም ለዚህ ችግር ሊዳርጉ ይችላሉ፡፡  
ከዚህም በተጨማሪ የዘር ሐረግ የሚመረመርበት DNA አሰራር በሚመለከት ሲጋራ ከማጤስ ባህርይ ጋር እንደሚገናኝ አጥኚዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌም ሲጋራ በጣም ከሚያጤሱ አባቶች የሚወለዱ ልጆች እና አባቶቻቸው በትውልድ ወይንም በዘር እንደሚገናኙ ለማወቅ የሚደረገ ውን የDNA ምርመራ በቀጥታ ወይንም በፍጥነት ምላሽ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡
የአባቶች አጫሽነት በወንድ ልጆች የልጅ መውለድ አቅም በመቀነስ ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያ ደርግ እሙን ሲሆን በዚህ የተነሳ ሴት ልጆችም ለአጭር ጊዜ ልጅ ያለመውለድ ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ። ስለዚህ ልጅ ያለመውለድ ችግር ከእናትየው ሲጋራ ማጤስ ጋር ብቻ ሊያያዝ እንደማይገባውና ይልቁንም በዚህ መነሻነት ይበልጥ እውነታውን ለማወቅ የሚያ ስችል ምርምር እንዲኖር ያስፈልጋል ይላሉ Jonatan Axelsson.
በአለም ዙሪያ ልጅ መውለድ ያልቻሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥንዶች የተለያዩ ጥናቶችን በአንክሮ እንደሚከታተሉ እሙን ነው፡፡ በጥናቶቹም የሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ በማተኮር ሁሉም ከእራሳቸው ገጠመኝ ጋር የሚያያዙ ምክንያቶችን ለማስወገድ ጥረት ያደርጋሉ። ጥናት አቅራቢዎቹም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ ልጅ ላለመውለድ ምክንያት የሚሆኑትን ጉዳዮች በመፈተሸ የተሻለ መፍትሔ የሚሉትን ይጠቁማሉ በቴክሳስ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንደጠቆሙት። በቅርብ በተደረገው ጥናት ወንዶች ልጅ እንዳያስረግዙ ምክንያት ከሚሆናቸው ውስጥ የወላጆቻቸውን በተለይም የአባቶቻቸውን የአኑዋኑዋር ዘይቤ የሚፈትሽበት እና እንደችግር የሚቆጠረውን ነገር በይፋ ለማሳየት ሞክሮአል።   
የወንዶች ልጅ የማስረገዝ ተፈጥሮአዊ ችሎታ መቀነስና ችግር የሚወገ ድበትን አቅጣጫ የሚያሳየው የምርምር ውጤት ሐኪሞች ለታካሚዎቻቸው የሚሰጡትን የምክር አገልግሎት ለመለየት የሚያስችል ነው፡፡ የዚህ ውጤትም ጥንዶቹ ልጅ ለመውለድ የሚያስችላቸውን ዘዴ እስኪያገኙ የሚፈጁትን ጊዜ ይቆጥባል፤የመንፈስ ጭንቀትን እና ገንዘብን ይቀንሳል፡፡ ይህ ለረጅም ጊዜ እርግዝናን ለሚጠብቁ ጥንዶች ትልቅ መፍትሔ ይሆናል። ስለዚህም ጥንዶች ልጅ ያለመውለድ ችግር ሲገጥማቸው ሐኪሞቻቸውን ማማከርና የችግሩን መንስኤ መፈተሸ እንዳለባቸው ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡   
ምንጭ፡- The University of
Texas at San Antonio.

Read 2282 times