Saturday, 15 December 2018 16:13

በኢትዮጵያ የሂውንዳይ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

       ከተቋቋመ 10 ዓመት ያስቆጠረው ማራቶን ኢንጂነሪንግ፤ የሂውንዳይ መኪኖች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሰሞኑን አስመርቋል፡፡ በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ  ታቅዶ የነበረው የፋብሪካ ግንባታው፤ በአመት ከ8 ወር ውስጥ ተጠናቆ መኪኖችን ማምረት እንደጀመረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ የኤሌትሪክ መኪና ለማምረት ማቀዱን፣የኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡
የሂውንዳይ መኪኖችን እያስመጣ ሲሸጥ የቆየው ማራቶን ኢንጂነሪንግ፤አሁን በአገር ውስጥ መገጣጠም በመጀመሩ ዋጋው ከ15-18 በመቶ እንደሚቀንስ ታውቋል፡፡ ፋብሪካው በቀን 36፣ በዓመት 10ሺ አውቶሞቢሎችን እንደሚያመርት የማራቶን ኢንጂነሪንግ ሊቀመንበር አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴና ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መልካሙ አሰፋ፣ከትላንት በስቲያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡  በአፍሪካ ሂውንዳይ መኪኖችን የመገጣጠም ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ሦስት አገራት ብቻ ናቸው ያለው አትሌት ኃይሌ፤ ይሄ የሚያሳየው ይችላሉ ብለው በእኛ ላይ እምነት ማሳደራቸውን ስለሆነ
ትልቅ ነገር ነው ብሏል፡፡     

Read 5921 times