Saturday, 19 May 2012 11:30

“ሶይ ኩባ” ለተማሪዎች ሊታይ ነው

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሩስያዊው አዘጋጅ ሚካኤል ካልቶዞቭ በኩባ የተሰራውና የ1964 እ.ኤ.አ ኩባ የፍቅር እና የሀገሪቱን ሁኔታ የሚያሳየው “ሶይ ኩባ” ፊልም ለፊልም ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ሌሎች ተመልካቾች ሊታይ ነው፡፡ የ135 ደቂቃ ፊልሙ ከነገ ወዲያ ከቀኑ 11 ሰዓት የሚታየው ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚኘው ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዥን አካዳሚ ሲሆን ታዳሚዎቹም የአካዳሚው ተማሪዎችና ሌሎች ፊልም ተመልካቾች እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ ትምህርት ቤቱ ይህን ዝግጅት የሚያቀርበው World Cinema Series በሚል መርሃ ግብሩ ሲሆን በዚህ መልኩ ዓለምአቀፍ እውቅና ያላቸው ፊልሞች በማሳየት ለመማርያና መወያያ ሲያውል ባለፉት ሦስት ዓመታት ለ74ኛ ጊዜ ነው፡፡

 

 

Read 933 times Last modified on Saturday, 19 May 2012 11:41