Saturday, 24 November 2018 12:47

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ይካሄዳል

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማኔጅመንት ባለሙያዎች ማህበር ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር በመተባበር `Recent developments in the construction industry` በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ በስቲያ ሰኞ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በኢሲኤ መሰብሰቢያ አዳራሽ የግማሽ ቀን ጉባኤ  ያካሂዳል፡፡
 በጉባኤው ላይ ከተለያዩ አገራት የሚመጡ እንግዶች የሚሳተፉ ሲሆን የኮንስትራክሽን ሚኒስትርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንደሚገኙም ታውቋል፡፡ በአጠቃላይ ከ500 በላይ ተሳታፊዎች በሚገኙበት በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከእንግሊዝ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲንጋፖርና ህንድ የሚመጡ ተወካዮች ተመክሮአቸውን እንደሚያጋሩ ተጠቁሟል፡፡

Read 1703 times