Monday, 12 November 2018 00:00

የአፍሪካ አገራት 1 ትሪሊዮን ዶላር በሚደርሰው አለማቀፍ ንግድ ያላቸው ድርሻ 15 በመቶ ብቻ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 አፍሪካ 1 ትሪሊዮን ዶላር ከሚደርሰው የአፍሪካ አመታዊ አለማቀፍ ንግድ ውስጥ የአህጉሪቱ አገራት ያላቸው ድርሻ 15 በመቶ ብቻ መሆኑን ኦልአፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡ የአፍሪካ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ ሰሞኑን ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ አፍሪካ አገራት በአመታዊው የአህጉሪቱ አለማቀፍ ንግድ ውስጥ ያላቸው ድርሻ 150 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብቻ ነው፡፡
የአገራቱ የንግድ ድርሻ አነስተኛ ሊሆን የቻለው አገራቱ በቂ የአለማቀፍ ንግድ ገበያ መረጃ ስለሌላቸውና ንግዱን የሚደግፍ በቂ መሰረተ ልማት ለመገንባት ባለመቻላቸው ነው ብሏል ተቋሙ፡፡ አንዳንድ አገራት የአፍሪካ የንግድ ስምምነትን አለመፈረማቸው የንግድ ተሳትፎ ድርሻቸውን ዝቅ እንዳደረገባቸውም ተቋሙ ኣስታውቋል፡፡

Read 2305 times