Monday, 12 November 2018 00:00

በሶማሌ ክልል የ2 መቶ ሰዎች የጅምላ መቃብር ተገኘ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

 የ200 ሰዎች የጅምላ መቃብር በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል አዋሣኝ አካባቢ መገኘቱን የገለፀው የፌደራል ፖሊስ፤ በጅምላ ተቀብረው የተገኙትን አስከሬኖቹ ማንነት ለመለየት እያደረገ ምርመራ እያደረገ መሆኑም አስታውቋል፡፡
ፖሊስ የጅምላ መቃብሩን ያገኘው በአሁን ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ ኡመር ላይ ተጨማሪ ምርመራዎች በሚያከናወንበት ወቅት መሆኑን ጠቁሟል፡፡
በሰዎች ግድያና ኢ-ሠብአዊ ድርጊቶች በመፈፀም ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አብዲ መሐመድ፤ በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ላለፉት 13 አመታት በክልሉ በርካታ ኢ-ሠብአዊ ተግባራት በዜጐች ላይ መፈፀማቸውን ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት በተለያዩ ጊዜያት ባወጧቸው ሪፖርቶች መጠቆማቸው ይታወሳል፡፡
አሁን ፖሊስ አግኝቸዋለሁ ያለው የጅምላ መቃብር አቶ አብዲና አስተዳደራቸው ከሚወቀሱባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር ስለመያያዙ ተጣርቶ ውጤቱ ለፍ/ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈርና ዜጐችን በተለያየ ዘዴ ማሰቃየትና ቶርች መፈፀም ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኘው የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት፤ ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርበው ተጨማሪ የአሥራ አራት ቀን ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡   

Read 6005 times