Print this page
Monday, 10 September 2018 00:00

86ኛው ግጥም በጃዝ የፊታችን ረቡዕ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 ዕለቱ ለአንጋፋዋ ከያኒ አለምፀሀይ ወዳጆ ተበርክቷል

     86ኛው ጦቢያ ግጥም በጃዝ የፊታችን ረቡዕ መስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
ዕለቱ ለአንጋፋዋ አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ የተበረከተ ሲሆን፤ ደበበ እሸቱ፣ አለምፀሀይ ወዳጆ፣ ነብይ መኮንን፣ ጌትነት እንየው፣ ሰርፀፍሬ ስብሃት፣ ተፈሪ አለሙ፣ የህናት አምባ ኳየር እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ “ኮሚቴው” የተሰኘ አጭር ተውነት በአርቲሰት ፍቃዱ ከበደ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ በምሽቱ የዘመኑ ወጣት ገጣሚያን በጋራ የሰሩትን ልዩ የዘመን መለወጫ ግጥም ለአንጋፋዋ አርቲስት ለተበረከተው 86ኛው ምሽት እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡


Read 4822 times