Saturday, 25 August 2018 13:23

የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ በመስከረም አጋማሽ ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(9 votes)

 “የአብዮታዊ ዲሞክራሲ” ርዕዮተ ዓለም ሊለወጥ ይችላል

    በነሐሴ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ በቀጣዩ መስከረም አጋማሽ ላይ እንደሚካሄድ ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ አባል ድርጅቶቹ የየራሳቸውን ጉባኤ ባለማጠናቀቃቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ኢህአዴግ በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በዋናነት ሰሞኑን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ምንጮች፤ ድርጅቱ ወደ አንድ ውህድ ፓርቲ የሚለወጥበት ጥናት ለጉባኤው እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡ በዚህ ጉባኤ ገዢው ፓርቲ ለበርካታ ዓመታት ሲመራበት የቆየው የ“አብዮታዊ ዲሞክራሲ” ርዕዮተ ዓለም ላይ ግምገማ እንደሚደረግና ድርጅቱ ርዕዮተ ኣለሙን ሊለውጥ እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፡- ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴን እና ህውሓት በመጪዎቹ ቀናት ጉባኤያቸውን ያካሂዳሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ድርጅቶቹ የስምና አርማ ለውጥ እንደሚያደርጉ እንዲሁም መተዳደሪያ ህገ ደንባቸውን ሊለውጡ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡


Read 11242 times