አሊስን
ውድ እግዚአብሔር
ቄስ ኮሊን ጓደኛህ ናቸው ወይስ በሥራ ጉዳይ ብቻ ነው የምታውቀው?
አኒታ
ውድ እግዚአብሔር
ክረምቱን ብጠብቀውም እስካሁን ተመልሶ አልመጣም፡፡ ብቻ እንዳትረሳው
ማርክ
ውድ እግዚአብሔር
ወንድሜ አይጥ ነው…አይጥ ልትሰጠው ይገባሃል…ሃሃ…ሃ
ዴቪድ
ውድ እግዚአብሔር
ትላንትና የሰራኸውን ቀስተደመና እስክመለከት ድረስ ብርቱካን ቀለም ከወይንጠጅ ጋር የሚስማማ አይመስለኝም ነበር፡፡ አሪፍ ነበር!
ሊዝ
ውድ እግዚአብሔር
ሰንበት ት/ቤት አንተ ሁሉም ቦታ እንዳለህ አስተምረውናል፡፡ ምን ያህል ትልቅ ነህ?
ጄሲ