“ሎል” በመጀመርያ ሳምንቱ ያስገኘው ገቢ ከ50ሺ ዶላር አይበልጥም፡፡በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ ለመጀመርያ ግዜ የታየው የሱፐርሂሮዎች ጀብደኛ ፊልም “ዘ አቬንጀርስ” በሰሜን አሜሪካ 200 ሚሊዮን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ አስመዝግቦ፣ አዲስ ሪኮርድ መያዙን ሮይተርስ ገለፀ፡፡ ፊልሙ በሰሜን አሜሪካ ገበያ በመጀመርያ ሳምንት ባስገባው ገቢ ሪኮርዱን የያዘው ከዓመት በፊት የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ክፍል በሰሜን አሜሪካ ያገኘውን የመጀመርያ ሳምንታዊ ገቢ በ30 ሚሊዮን ዶላር በመብለጡ ነው፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መታየት ከጀመረ ወር ያለፈው “ዘ አቬንጀርስ” በዓለም ዙርያ የሰበሰበው ገቢ 641 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡