በአንድ ምሽት ለሚሰራው የሙዚቃ ኮንሰርት 600ሺ ዶላር የሚከፈለው ቢበር፤ በትዊተር ድረገፁ 21 ሚሊዮን ተከታታዮች ሲያፈራ በፌስ ቡክ አድራሻው ደግሞ ከ41 ሚሊዮን በላይ ወዳጆች ያለው መሆኑን የጠቀሰው “ዘ ቢዝነስ ኢንሳይደር”፤ ይህም በመላው ዓለም ያለውን ተወዳጅነትና ተፈላጊነት እንደጨመረለት አብራርቷል፡፡ ጀስቲን ቢበር ከሁለት ዓመት በፊት የሰራውና የህይወት ታሪኩን የሚያሳየው “ኔቨር ሴይ ኔቨር” የተባለው ፊልሙ፤ በዓለም ዙርያ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ያመለከተው “ዘ ቢዝነስ ኢንሳይደር”፤ በ120 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል የሚያንቀሳቀሰው የሽቶ አምራች ኩባንያም ለስኬታማነቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከተለት ጠቅሷል፡፡