Saturday, 12 May 2012 09:00

ቦቢ ብራውን የልጁን እናት ያገባል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

አንጋፋው የአርኤንድቢ የራፕ ሙዚቃ ድምፃዊና ዳንሰኛ ቦቢ ብራውን፤ በመጪው ወር ትዳር ሊመሰርት መሆኑን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ የ43 ዓመቱ ቦቢ ብራውን ጋብቻ የሚፈፅመው ከሁለት ዓመት በፊት ቀለበት ካሰረላት እጮኛው አሊሻ ኢትሪጅድ ጋር እንደሆነ ታውቋል፡፡ የቀድሞ ሚስቱ ዊትኒ ሂዩሰተን በድንገተኛ አደጋ ህይወቷ ያለፈው ከሦስት ወራት በፊት ነው፡፡  ለሦስት ዓመታት በፍቅር ጓደኝነት አብራው የቆየችው አሊሻ ወንድ ልጅ የወለደችለት ሲሆን ጋብቻቸውን በሀዋይ እንደሚፈፅሙ ተገልጿል፡፡

ከሳምንት በፊት በቀድሞ ሚስቱ ዊትኒ ሃውስተን ድንገተኛ አሟሟት ላይ ለ”ቱዴይሾው” ቃለምልልስ የሰጠው ቦቢ ብራውን፤ ለ14 ዓመት በትዳር አብራው የኖረችው ዊትኒ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ለመሆኗ ምክንያት በመሆኑ የተሰማውን ፀፀት ቢገልፅም ለደረሰባት ድንገተኛ ሞት ተጠያቂ መደረጉን ግን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በሙሉ ስሙ ሮበርት ባሪስፎርድ ተብሎ የሚጠራው ቦቢ ብራውን፤ ለ34 ዓመታት በቆየበት የሙዚቃ ኢንዱስትሪ አራት አልበሞችን በመስራትከ8 ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ለመሸጥ ችሏል - በመላው ዓለም፡፡

 

 

 

 

 

Read 1384 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:04