Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 08:54

በሞባይል ስርቆት የተጠረጠረ በድንጋይ ተደብድቦ ሞተ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በደቡብ አፍሪካ ከአንዲት ሴት ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቋል ተብሎ የተጠረጠረ ግለሠብ በድንጋይ ተደብድቦ ሞተ፡፡  ደቡብ አፍሪካ በሰሜናዊ ፓሎክዋኔ ከተማ አንዲት ሴት ሞባይልዋ በመሠረቁ ባሰማችው ጩኸት የተሰባሰቡ ሰዎች ስልኳን ሰርቋል ያሉትን ሠው አባረው በመያዝ ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ በድንጋይ እንደወገሩት ፖሊስ ገልጿል፡፡

ፖሊስ ግለሰቡን ሊያነሳው ሲሄድ አካሉ በድንጋይ እና በሌሎች ነገሮች ተሸፍኖ እንደነበር ያመለከተው ፖሊስ፤ በገዳዮቹ ላይ ምርመራ መጀመሩን ጨምሮ ገልጿል፡፡ ወንጀል በተንሠራፋባት ደቡብ አፍሪካ፤ ህብረተሰቡ በግብታዊነት የሚወስደው እርምጃ የተለመደ እንደሆነ የጠቆመው ፖሊስ፤ በዓመት በአማካይ አርባ ሶስት ሠዎች በዚህ መንገድ ህይወታቸው እንደሚያልፍ አመልክቷል፡፡

 

Read 3247 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 08:58