Sunday, 06 May 2012 15:07

ማህበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ መፃሕፍትና ፊልሞችን ያስመርቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር በሚገኘው ማህበረ ቅዱሳን ዘንድሮ የተዘጋጁ 10 መፃሕፍትንና ሌሎች 10 መንፈሳዊ ፊልሞችን ያስመርቃል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 አምስት ኪሎ ባለው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዲሱ አዳራሽ የሚመረቁት መፃሕፍትና ፊልሞች ማህበሩ በዘንድሮው ዓመት ካሳተማቸው 17 መፃሕፍት እና 21 የኦዲዮ ቪዥዋል ውጤቶች መካከል የተመረጡ ናቸው፡፡ በመፃሕፍት ዝግጅቱ ደራሲ ፀሃይ መልአኩ፣ ዲያቆን ማለዳ ዋስይሁን፣ ዲያቆን ታደለ ፈንታ፣ የማህበሩ መፃሕፍትና ዝግጅት ክፍል እና ሌሎትም ይገኙበታል፡፡ ከድምፅ እና ምስል /ኦዲዮ ቪዥዋል/ ውጤቶች መካከልም በቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም፣ በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ፣ እና በቀሲስ ፋሲል ታደሰ የተዘጋጁት ተጠቅሰዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርአቱ ላይ ማህበሩ ዘመናዊ የቤተክርስትያን ፅሑፎችን በተመለከተ ያለውን ሚና የሚዳስስ እንዲሁም የማህበሩን ሕትመት ሥርጭት የተመለከቱ የጥናት ፅሑፎች እንደሚቀርቡም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላም በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና በተለያዩ ምሁራን የቀረቡ የጥናት ጽሑፎች የተካተቱበት ቁጥር 100 መጽሐፍ እንደሚመረቅ የፌደራሊዝም ጥናት ተቋም አስታወቀ፡፡ ጥናቶቹ በአምስተኛው ዓለምአቀፍ የፌደራሊዝም ጉባኤ የቀረቡ ናቸው፡፡ በጥናቶቹ ሕትመት ተቋሙ ከፎረም ኦፍ ፌደሬሽንስ የአፍሪካ ዳይሬክቶሬት ጋር ተባብረው በትብብር እንደሰሩ ታውቋል፡፡ መጽሐፉ ነገ በተቋሙ ሲመረቅ በCIDA ካናዳ ድጋፍ የተሰራ ኮምፒዩተር ማዕከልም አብሮ እንደሚመረቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 4840 times Last modified on Sunday, 06 May 2012 15:12