Sunday, 06 May 2012 15:04

“የመለስ አምልኮ” ለገበያ ቀረበ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(2 votes)

በ”ፍትህ” ጋዜጣ መስራችና ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የተዘጋጀው “የመለስ አምልኮ” የተሰኘ ፖለቲካዊ መፅሃፍ ሰሞኑን ለገበያ ቀረበ፡፡ ፀሃፊው በጋዜጣው ላይ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ፖለቲካዊ ፅሁፎቹን በማሰባሰብ በመፅሃፍ መልክ ተደራጅተው እንደታተሙ በመግቢያው ላይ ጠቅሷል፡፡ በመፅሃፉ ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን፣ ፖለቲከኞችንና አጠቃላይ የአገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ የሚተቹና የሚነቅፉ ፅሁፎች ተካትተዋል፡፡የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለመፅሃፉ በሰጡት አስተያየት “ተመስገን ደፋርና ለአገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በጣም ተቆርቋሪ መሆኑን ከፅሁፎቹ በግልፅ እናያለን፡፡ ያለውን እውነታ ሳይፈራና ሳይደባብቅ ይናገራል፡፡

ሂስ መስጠት ብቻ ሳይሆን በምክር መልክ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ይገልፃል” ብለዋል፡፡ በአምስት ክፍሎች የተከፋፈሉ 32 ፖለቲካዊ ፅሁፎችን ያካተተው ባለ 255 ገፆች መፅሃፍ በ39 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ አንዳንድ አዟሪዎች ዋጋውን  እየሰረዙ  ጭማሪ እንደሚያደርጉ የገለፀው አሳታሚው አንባቢያን ከ39 ብር በላይ እንዳይገዙ መክሯል፡፡

 

 

 

Read 2274 times Last modified on Sunday, 06 May 2012 15:07