Print this page
Sunday, 06 May 2012 14:56

በ”ቶፕ ገን 2” ቶም ክሩዝ ተደነቀ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

ቶም ክሩዝ የሚተውንበት “ቶፕ ገን 2” ፊልም በቀረፃ ላይ መሆኑን ሎስአንጀለስ ታይምስ ገለፀ፡፡ የፊልሙ የመጀመርያው ክፍል ከ26 ዓመት በፊት ለእይታ መብቃቱን ያስታወሰው ጋዜጣው፤ በአጠቃላይ 354 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ጠቅሷል፡፡ በ”ቶፕ ገን” ፊልም ላይ የአሜሪካ ተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ የሰራው ቶምክሩዝ የተዋጣለት ትወና እንዳሳየ የዘገበው ሎስ አንጀለስ ታይምስ ተዋናዩ በፊልሙ ላይ የመስራት ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ሲገልፅ እንደነበር አስታውሷል፡፡

በተያያዘ ዜና ቶም ክሩዝ የሚተውንበት የ”ሚሽን ኢምፖሲብል” 5ኛ ክፍል ሊሰራ እንደሚችል ታውቋል፡፡ አምና የዱባይን ትልቁን ፎቅ ቡርጃ ካሊፋን በመንጠላለጠል አስገራሚ ትወና በማሳየቱ የተደነቀው ቶም ክሩዝ የ”ሚሽን ኢምፖሲብል” 4ኛ ክፍል የሆነውና “ዘ ጎስት ፕሮቶኮል” በሚል ንዑስ ርእስ በቀረበው በዚህ ፊልሙ በመላው ዓለም የተሰበሰበው ገቢ  694 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡ በሌላ በኩል በብሮድዌይ ከሦስት ሳምንት በፊት መታየት በጀመረው “ሮክ ኦፍ ኤጅስ” በተባለ ሙዚቃዊ ቲያትር ላይ የሚተውነው ቶም ክሩዝ፤ በአተዋወን ብቃቱ አድናቆትን እንዳተረፈ “ዘ ሃፊንገተን ፖስት” ዘግቧል፡፡ በሙዚቃዊ ቲያትሩ ላይ ቶም ክሩዝ የሮክ ሙዚቀኛ ሆኖ የሚጫወት ሲሆን አሌክ ባልድዊንና ራስል ብራንድ አብረውት እንደሚተውኑ ታውቋል፡፡ ቶም ክሩዝ ከ30 በላይ ፊልሞች ላይ የሰራ ድንቅ የሆሊውድ ኮከብ ነው፡፡

 

Read 1191 times Last modified on Sunday, 06 May 2012 14:59