Saturday, 28 April 2012 13:19

“አለምገና ታነባለች” ነገ ይጠናቀቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ጌት ፈርኒቸር እና እንጨት ሥራ ድርጅት ያዘጋጀውና መጽሐፍ በማንበብ የዝግጅቱ መግቢያ የሚገኝበት የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ በዓለምገና ከተማ ይጠናቀቃል፡፡ በአራት ዙር የተካሄደው ውድድር አሸናፊዎች “አለምገና ታነባለች” በሚል በጐ ሃሳብ የሚሸለሙት መጽሐፍ እንደሆነ የድርጅቱ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌቱ በቀለ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ድርጅቱ በዘጠኝ ወራት 20ሺህ ብር የሚያወጡ መፃሕፍት መሸለሙንና ባላቸው አነስተኛ ቤተመፃሕፍት ብዙ አንባቢ አለመኖሩ አሳስቧቸው ሽልማቱን እንዳቀዱና ከከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ጋር በጋራ እንደሚሰሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 1088 times Last modified on Saturday, 28 April 2012 13:21