Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 April 2012 13:08

ሊዮኔል ሪቼ ቢልቦርድን እየመራ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ62 ዓመቱ ሊዮኔል ሪቼ ከ21 ቀናት በፊት ለገበያ ባበቃው “ታስኪጅ” የተሰኘ አዲስ አልበሙ፤ የቢልቦርድ ምርጥ 200 አልበሞችን ደረጃ በአንደኛነት እየመራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡በሶስት ሳምንት ውስጥ ከ423ሺ በላይ ቅጂዎች የተሸጠው የሊዮኔል ሪቼ 11ኛ አልበም፤ በካንትሪ የሙዚቃ ስልት ከምርጥ የአሜሪካ ሃገረሰብ አቀንቃኞች ጋር የተሰሩ 13 ዘፈኖቹ  ለገበያው መሟሟቅ ምክንያት እንደሆኑ ተጠቁሟል፡፡ከ35  ሚሊዮን በላይ የአልበም ቅጂዎች ሽያጭ በመላው ዓለም ያስመዘገበው ሊዮኔል ሪቼ፤ ላለፉት 45 ዓመታት የፖፕና ሶል ሙዚቃዎችን አዋህዶ በመጫወት ዛሬም ድረስ ዝነኛ የሆነ ጥቁር አሜሪካዊ አርቲስት ነው፡፡

እንደ ሮይተርስ ዘገባ፤ ሊዮኔል ሪቼ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደሞሮኮ ሊቢያ ዱባይና ኢራቅ በመሳሰሉ የአረብ አገራት ተወዳጅ ድምፃዊ ሆኗል፡፡በተያያዘ ለዘንድሮ የቢልቦርድ ሙዚቃ አዋርድ የታጩ አርቲስቶች ዝርዝር ሰሞኑን ይፋ ሆነ፡፡ በዋናዎቹ  ሰባት የሽልማት ዘርፎች እንግሊዛዊቷ አዴሌ በቀዳሚነት በመታጨት ትኩረት ስታገኝ ሌዲ ጋጋ እና ሪሃና እያንዳንዳቸው በ13 የሽልማት ዘርፎች እጩዎች ሆነው ይፎካከሯታል፡፡ ሽልማቱ በ2012 በቢልቦርድ የሙዚቃ ሽያጭ ደረጃ ሰንጠረዥ በነበረ ውጤትና የእጩዎቹ የአልበም ስራዎች በዲጂታል ገበያው ካላቸው ስኬት አንፃር በማወዳደር ከወር በኋላ ለአሸናፊው ይሰጣል፡፡

 

 

 

 

Read 1424 times Last modified on Saturday, 28 April 2012 13:10