ባለፉት ስምንት ዓመታት በክሪስቶፈር ኖላን ተሰርተው ለእይታ የበቁት ሁለት ክፍል የባትማን ፊልሞች “ባትማን ቢጊንስ” እና “ዘ ዳርክ ናይት” የተባሉት ሲሆኑ የመጀመርያው በ150 ሚ. ዶላር በጀት ተሰርቶ በአጠቃላይ 372 ሚ. ዶላር ሲገኝበት በ185 ሚሊዮን ዶላር የተሰራው ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዓለም አቀፍ ገቢ እና 16 ሚሊዮን የዲቪዲ ሽያጭ አግኝቷል፡፡ ሌጀንዳሪ ፒክቸርስ እና ዋርነር ብሮስ በትብብር የሚሰሩት ሦስተኛው “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” በአጠቃላይ የሚፈጀው ወጪ 250 ሚ. ዶላር እንደሚደርስ ኤልኤ ታይምስ ጠቁሟል፡፡ የፊልሙ መሪ ተዋናዮች ክርስትያን ቤል እና ኬሲ አፍሌክ ሲሆኑ ጋሪ ኦልድ ማን፤ ማይክል ኬንና ሞርጋን ፍሪማን በረዳት ተዋናይነት ይሳተፉበታል፡፡ ፊልሙን በህንድ፤ በለንደን፤ በግላስኮው፤ በኒውዮርክ ፤ በኒውጀርሲ እና በፒትስበርግ በመዘዋወር የቀረፀው ክሪስቶፈር ኖላን፤ የምስል ጥራቱን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ፣ ውዶቹን የአይማክስ ካሜራዎች እንደተጠቀመ ለማወቀ ተችሏል፡፡