Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 07 April 2012 09:31

ለሕግ ታራሚዎች መፃሕፍት ይሰበሰባሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“እኛ የምንለውን ቤተ መፃሕፍት እንገንባ” በሚል መርህ ለሕግ ታራሚዎች መገልገያ የሚሆኑ መፃሕፍት ሊሰባሰቡ ነው፡፡ አሰባሳቢዎቹ እስካሁን 400 መፃሕፍት ያሰባሰቡ ሲሆን ሰኞ ከቀኑ 11፡30 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር በሚቀርብ ዝግጅት ተጨማሪ ከ1200 በላይ መፃሕፍት ለማሰባሰብ ጥረት እንደሚደረግ የሀሳቡ ጠንሳሽ ሲስተር ሊንዳ ደበበ ወልደሰማያት ለአዲስ አድማስ ተናግራለች፡፡

እንደ እርስዋ ገለፃ አሁን እየተሰበሰቡ ያሉት መፃሕፍት ቃሊቲ ለሚገኘው ማረሚያ ቤት እንደሚሰጡና ማረሚያ ቤቱ በራሱ ማጓጓዣ መፃሕፍቱን ለታራሚዎቹ አብያተ መፃሕፍት ለማድረስ ቃል ገብቷል፡፡ ከጥበብ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለሚቀርበው ዝግጅት ጃፋር መፃሕፍት መደብር፣ ቢጂአይ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር፣ እና ኬር ማስታወቂያና ፕሮሞሽን እገዛ አድርገውለታል፡፡ ሰኞ ምሽት በትያትር ቤቱ ለሚቀርበው ኪነጥበባዊ ዝግጅት መግቢያ ከወትሮው የተለየ ሆኖ ታዳሚዎች መፅሐፍ እንደ ትኬት እንደሚጠቀሙም ማወቅ ተችሏል፡፡ ግጥምና ሙዚቃ፣ መጣጥፍ፣ ወግ፣ አጭር ተውኔት፣ ሥዕል፣ ቅርፃ ቅርፅ የሚቀርቡ ሲሆን ከእለቱ እንግዶች መካከልም ጌትነት እንየው፣ በቀለ መኮንን፣ ስለሺ ደምሴ፣ ዳዊት ፍሬው፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ባንቺአየሁ ዓለሙ፣ ምልዕቲ ኪሮስ ይገኙበታል፡፡

 

 

Read 1915 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:33