Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 07 April 2012 09:30

“ሩጫዬን ጨርሻለሁ” ፊልም ነገ “ፍቅርና ሕይወት“ ዛሬ ይመረቃሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ደራሲና ዳይሬክተር ሙላለም ጌታቸው የሠራው “ሩጫዬን ጨርሻለሁ” ፊልም በሳሚ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ድሮፕስ ፊልም ፕሮዳክሽን ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን ይኸው ፊልም ነገ እንደሚመረቅ ሳሚ ፊልም ፕሮዳክሽን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ እና በአዳማ የሚመረቀውን ፊልም ሠርቶ ለማጠናቀቅ አራት ወራት ፈጅቷል፡፡ በ98 ደቂቃ አስቂኝ የፍቅር ፊልሙ ላይ ሳሮን ተፈሪ (ሚሶ ነጋያ)፣ ሙላለም ጌታቸው፣ ዘላለም ይታገሱ፣ ጀምበር አሰፋ፣ ምትኩ በቀለ፣ ብርሃን ተስፋዬ፣ ኢየሩሳሌም ሽመልስ፣ እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡

በሌላም በኩል ብርሃን ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኤቢ ፊልም ፕሮዳክሽን ተባብረው ያቀረቡትን አለልኝ ብርሃኑ ፅፎት ፍፁም ካሳሁን ያዘጋጀው “ፍቅር እና ሕይወት” ፊልም ዛሬ በሲኒማ እምቢልታ ይመረቃል፡፡ ከቀኑ 7፡30 የሚመረቀውን የፍቅር ድራማ ፊልም ለመሥራት ስድስት ወራት ፈጅቷል፡፡ በ80 ደቂቃ ፊልሙ ላይ ሕሊና ጌታቸው፣ ሚፍታ ዘለቀ፣ ኢየሩሳሌም ሽመልስ፣ ሶስና በለጠ፣ ኤፍሬም የኋላ እሸት ስሜነሽ በቀለ እና ሌሎችም በትወና ተሳትፈዋል፡፡

 

Read 3150 times