Saturday, 07 April 2012 09:23

“መቅዲ ሾው” ነገ በኢቢኤስ ይጀመራል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ትስስር”፣ “የአዳም ገመና”፣ “ዘራፍ” በተሰኙት ፊልሞቿ የምትታወቀው መቅደስ ፀጋዬ በኢትዮጵያን ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ኢቤኤስ) አዲስ የቴሌቪዢን ዝግጅት ልትጀምር ነው፡፡ ነገ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ቀርቦ በድጋሚ ሐሙስ በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀርበው “መቅዲ ሾው” የተባለውይኸው ዝግጅት የአንድ ሰዓት ርዝመት አለው፡፡

በመቅዲ ፕሮዳክሽን የሚቀርበው ዝግጅት፣ የአየር ሰዓቱን በነፃ ማግኘቱንና ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር 50% የማስታወቂያ ገቢ መጋራት በሚል እንደተስማሙ የገለፀችልን የፕሮዳክሽኑ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፈይዛ ሀይሩ፤ ለቀጣይ ሦስት ወራት የሚሆነው ዝግጅት ቀረፃ በአዲስ አበባው ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል መጠናቀቁን ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ገልፃለች፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ የመጀመሪያ ሳምንት አርቲስት አብርሃም ወልዴ፣ በሁለተኛው የሀበሻ ካፒታሉ አቶ እስክንድር ደስታ፣ በሦስተኛው የንግድ ምክር ቤቷ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሙሉ ሰሎሞን እንግዶች መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 1759 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:30