Saturday, 07 April 2012 09:17

የዩሪ ጋጋሪ የጠፈር ጉዞ ሐሙስ ይታሰባል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

የዓለም የመጀመሪያው ጠፈርተኛ ሩስያዊው ዩሪ ጋጋሪ ወደ ጠፈር የተጓዘበት 51ኛ ዓመት በመጪው ሐሙስ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል አስታወቀ፡፡ በዚሁ ቀን ከቀኑ 11 ሰዓት ፒያሳ በሚገኘው የሩስያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል ፑሽኪን አዳራሽ ከጠፈር እና ከምድር የተነሱ ፎቶግራፎች በአውደርእይ መልክ ለሕዝብ ይታያሉ፡፡

ለአውደርእዩ ታዳሚዎች የሩስያ ባህላዊ ሻይ አፈላል በሳሞቫር እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ ለሁለት ሳምንት ክፍት ሆኖ የሚቆየውን አውደርእይ በመተባበር ያዘጋጁት ማዕከሉና የኢትዮጵያ ሕዋ ሳይንስ ማህበር ናቸው፡፡

 

 

Read 1760 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:22