Saturday, 07 April 2012 09:15

“እውነት ማለት የኔ ልጅ የግጥም መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(1 Vote)

“የኢትዮጵያ የኩባንያ ሕግ” ተመረቀ

በዶክተር በድሉ ዋቅጅራ የተዘጋጁ ግጥሞች የተካተቱበት “እውነት ማለት የኔ ልጅ” መድበል ዛሬ ከጧቱ 3፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በኪነጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚመረቅ አስመራቂው ዛጐል ቤተመፃሕፍት አስታወቀ፡፡ ዶ/ር በድሉ ካሁን ቀደም “ፍካት ናፋቂዎች” በተሰኘው የግጥም መጽሐፉ እንዲሁም “ቋንቋን በሥነጽሑፍ ማስተማር” በተሰኘ ሌላ መጽሐፉ ይታወቃል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ አቶ ፈቃዱ ጴጥሮስ የፃፉት “የኢትዮጵያ የኩባንያ ሕግ” መጽሐፍ ሐሙስ ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ፋኩልቲ “ሩም 8” ተመረቀ፡፡ 280 ገፆች ያሉትን መጽሐፍ ምርቃት ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ወጣት የሕግ ባለሙያዎች ማህበር መሆኑን ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ይበልጣል ተሻገር ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

 

 

Read 1607 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:17