Saturday, 07 April 2012 09:15

“ፓሽን” መጽሔት ዛሬ ገበያ ይወጣል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ማርሻል ፕሮሞሽን ያዘጋጀው ወርሃዊ የስፖርት መጽሔት “ፓሽን“ የመጀመሪያ እትም ከዛሬ ጀምሮ ገበያ ላይ እንደሚውል አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ ዋና ትኩረቱን ለሀገር ውስጥ ስፖርት ያደረገው መጽሔት የውጭ ዘገባዎችንም ያቀርባል፡፡ በመጽሔቱ ላይ በሀገር ውስጥና በውጪ ሐገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎች በአምደኝነት እንደሚጽፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከአምደኞቹ መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሙላለም እጅጉ፣ ኢንስትራክተር አብርሃም ተክለሃይማኖት እና የካፍ ኢንስትራክተር ዳኛ ሽፈራው እሸቱ ይገኙባቸዋል፡፡

 

 

Read 1120 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:17