Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 07 April 2012 09:09

የአሸር 7ኛ አልበም ከሦስት ወር በኋላ ይለቀቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰባት የግራሚ ሽልማቶችን የወሰደው አሸር፤ 7ኛ አልበሙን ከሦስት ወራት በኋላ ለገበያ እንደሚያበቃ ኤምቲቪ ኒውስ ገለፀ፡፡ “ሉኪንግ ፎር ማይሰልፍ” የተባለውን የአሸር አልበም አርኤሲ ሪኮርድስ የሰራው ሲሆን አልበሙ ገበያውን የመቆጣጠር አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡በሙሉ ስሙ አሸር ቴሪ ራይሞንድ 5ኛ ተብሎ የሚጠራው የ33 ዓመቱ የአርኤንድቢ ኮከብ   አቀንቃኝ በሶል እና ፖፕ የሙዚቃ ስልቶችም ስኬታማ ሲሆን በትወና እና በዳንስ ችሎታዎቹም ከፍተኛ ዝና ተቀዳጅቷል፡፡

በሙዚቃ ስራው 20 ዓመታትን ያስቆጠረው አሸር፤ ከሁለት ዓመት በፊት  ለገበያ እስካበቃው “ራይሞንድ ቨርሰስ ራይሞንድ” የተባለ 6ኛ አልበሙ ድረስ በዓለም ዙርያ 65 ሚሊዮን ቅጂዎችን ሸጧል፡፡ አሸር ሰሞኑን ከእንግሊዛዊቷ ድምፃዊት አዴል ጋር ሙዚቃ መስራት መፈለጉን የተናገረ ሲሆን “ኮንፌሽንስ” በተባለ አልበሙ በአመት ውስጥ በሰሜን አሜሪካ ገበያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎችን በመሸጥ ያስመዘገበውን ክብረወሰን ለመስተካከል አቅም ያላት አርቲስት መሆኗንም መስክሮላታል፡፡

 

 

 

Read 1314 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:10