Wednesday, 04 April 2012 10:51

በቀጣይ ዓመት የህዳሴ ፌደራል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

ዋንጫ ይዘጋጃል   አቶ ሳህሉ ገ/ወልድ የኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት

በተሳትፎው የተፈጠረብኝ ስሜት ሁሉም የተሰማው ነው፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እንደምታስተውለው ንቅናቄው ህዝባዊ ነው፡፡ ይህን ከፍተኛ ሞገድ በኋላ መንግስት ሊያስተባብረው ሞክሯል፡፡ የህዝብ ንቅናቄው ቀድሞ ወጥቷል ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን መንግስት ይህን በስፋት አደራጅቶ ለማጠናከር ነው የተነሳው፡፡ ይህ የተደራጀ እንቅስቃሴ በብዙ ዘርፍ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ ስፖርት አንዱ የልማት አካል ነው፡፡ ስፖርቱ የህዳሴው አካል ነው፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ አገራችን ከድህነት ለማውጣት ብሎም ድህነትን ለማስቀረት በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ ስፖርት ቦታ እንዲያገኝ በመደረጉና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በእግር ኳሱ ዙርያ መጥተው ተሰባስበው በህዝቡ ስሜት ለመፍጠር በመሞከራችን እንደግለሰብም እንደፌዴሬሽንም በጣም ያስደስተናል፡፡ በተረፈ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አንደኛ ዓመት በስፖርት ለማክበር የተፈጠረው አጋጣሚን ወደፊትም ተጠናክሮ የመንግስት ሃላፊዎች በየደረጃቸው የጤና ቡድን አቋቁመው ራሳቸውን እንዲጠቅሙ ስፖርቱንም እንዲደግፉ ለማስቻል ፍላጐት አለን፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የተለያዩ  አብይ  አብይ ኮሚቴዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ኮሚቴዎች አንዱ የስፖርት እና የአርቲስቶች እንቅስቃሴን የሚያከናውን ንዑስ ኮሚቴ ነው፡፡ ስለዚህም በዚህ ዙርያ ስፖርት ኮሚሽን፤ የእግር ኳስ እና የአትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ያሉበት ኮሚቴ እየሰራ ነው፡፡ በትጥቅ አቅርቦት በውድድር ዝግጅት እና በሌሎችም እየተሳተፈ ነው፡፡የህዳሴው ግድብ ለከልማታችን አንዱና አንኳር መሳርያ አቅማችን ነው፡፡ እንዲህ አይነት መሳርያዎች በየሂደታቸው መቋቋማቸው አይቀርም፡፡ አሁን በተፈጠረው መድረክ ዋናው ቁምነገር ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፡፡ ይልቁንስ ህብረተሰቡን በአንድነት ለማነሳሳትና መነቃቃትን ለመፍጠር የሚደረግ ነው ዘንድሮ የህዳሴው ካፕ ተብሎ የተጀመረው ውድድር በቀጣይ ዓመታት ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡናን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ክለቦችን በማሳተፍ የህዳሴ ፌደራል ዋንጫ በሚል በትልቅ ዝግጅት ውድድር ለማካሄድ እቅድ አለ፡፡ በየዓመቱ ልንቀጥለው እንፈልጋለን፡፡

 

 

Read 2956 times Last modified on Wednesday, 04 April 2012 10:54