Wednesday, 04 April 2012 08:28

የደስታ ቀን [ናውሩዝ (ፊስት)]

Written by  ከበደ ደበሌ ሮቢ
Rate this item
(1 Vote)

ናውሩዝ የኢትዮጵያ ባሃኢዎችና የመላው ዓለም ባሃኢዎች የደሥታ ቀን ወይም ፊስት ነው፡፡ ባለፈው ማክሠኞ መጋቢት 12 ቀን 2004 ዓ.ም ናውሩዝ በመላው ኢትዮጵያና በመላው ዓለም ባሃኢዎች ዘንድ ከፍ ባለ ድምቀት ተከብሮ ውሎአል፡፡ በባሃኢ እምነት (Bahaai Faith) የዘመን አቆጣጠር (Calendar) በዓመት ውስጥ አሥራ ዘጠኝ ወራት አሉ፤ ባሃ (ድምቀት) ጀላል (ክብር ወይም ፀጋ) ጃማል (ውበት) አዛማት (ታላቅ) ኑር (ብርሀን) ራህማት (ምኅረት) ካሊማት (ቃል) ወይም ቃላት ካማል (ፍፅምና) አሥማ (ስሞች) ኢዛት (ኃይል) ማሺያት (ፈቃድ) ኢልም (እውቀት) ኩድራት (ሥልጣን) ካውል (አንደበት) ማሣኢል (ጥያቄዎች) ሽራፊ (ክብር) ሡልጣን (ገዢነት) ሙልክ (ግዛት) አላዕ (ከፍተኛነት) … የሚሠኙ ናቸው የባሃኢ ወራት፡፡ አንድ ወር አሥራ ዘጠኝ ቀናት አሉት፡፡ በዓመት ውስጥ ካሉት አንዱ ወር የፆም ወር ነው፡፡ አሥራ ዘጠኝ ቀናት የፆሙ ባሃኢዎች ፆማቸውን የሚፈቱበት ዕለት ነው ናውሩዝ፡፡ ልክ ለክርስቲያኖች፡- ፋሢካ፤ ለሙስሊሞች፡- ኢድ ሙባረክ (የሮመዳን ፆም ፍቺ) እንደምንለው፡፡ የዓመቱ የመጀመሪያው ቀንም ነው ናውሩዝ፡፡ አዲስ ዓመት የሚጀመርበት፤ አሁን በባሃኢ የዘመን አቆጣጠር 169ኛው ዓመት ላይ እንገኛለን፡፡
የባሃኢ እምነት የአንድ መቶ ስልሣ ዓመታት ዕድሜ ያለው በመላው ዓለም የተሠራጨ (የተዳረሠ) ከእስልምናና ከክርሥትና አንፃር ጥቂት ምዕመናን ያሉት ሃይማኖት ነው፡፡ ለክርሥትና፡- ጌታ ኢየሡሥ ክርሥቶስ፤ ለእሥልምና፡- ነቢዩ መሀመድ፤ ለኢንዱኢዝም፡- ስሪ ክሪሽና … እንዳሉት ሁሉ፤ ለባሃኢ እምነት ባሃኡላህ በሚል መጠሪያ የሚታወቅ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ (The messenger of God) አለው፡፡ ባኻኡላህ በእግዚአብሔር መልዕክተኝነት በጥንታዊቱ ፋርስ (ፐርሺያ) በአሁኒቱ ኢራን ከመከሠቱ አስቀድሞ፤ የእርሡን መምጣት አስቀድሞ ለፋርሥ ህዝቦች የገለፀው ባብ የተሠኘ በነቢይ ልኬት የሚሠላ ኢራናዊ ነው፡፡ ባብ በፋርሥ ቋንቋ፡- በር (መግቢያ) ማለት ሲሆን፤ ባሃኡላህ ደግሞ፡- የእግዚአብሔር ክብር (The Glory of God) ማለት ነው፡፡ በዛሬው ዘመን በመላው ዓለም የሚገኙ ባሃኢዎች ሠላምታ ሲለዋወጡ፡- አላህ ኡ አብሀ ተባብለው ነው፡፡ ትርጓሜውም፡- እርሡ ከተከበሩት ሁሉ በላይ እጅግ የተከበረው ነው፤ He is The most Glorious ማለት ነው፡፡
ባሃኡላህ፡- ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ከነበረ ቤተሠብ የተወለደ ሲሆን፤ ገና በወጣትነቱ የቤተሠቡን ፈለግ በመከተል ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣንነት ታጭቷል፤  ይሁንና ዝንባሌውና የህይወት ጥሪው  ለተለየ ዓላማ በመሆኑ፡- ተውት … ነው ያሉት፤ ምንም እንኳን ልረዳው የማልችል ቢሆንም ከዚህ (ከታጨበት) ዓላማ የላቀ ተልዕኮ እንዳለው አልጠራጠርም …፡፡ ባሃኡላህ በጉርምሥና የዕድሜ ዘመኑ በፋርሥ ምድር በእግሩ በመጓዝ ላይ እያለ ሙሥጠፋ የተባለ ከአሁን ቀደም የማያውቀው ባህታዊ መንገድ ላይ አግኝቶት፡- አንተ የዕውነት ብርሀን ነህ … አለው፤ አንተ የመመሪያ ፀሀይ ነህ ራሥህን ለሌሎች ግለፅ …
በዚህች ዓለም ታሪክ ውስጥ በአስተሣሰባቸው ምክንያት ከተሠደዱና ከተሣደዱ እንዲሁም በእሥር ቤት ከማቀቁ ታላላቅ ሠብዕናዎች አንዱ ባሃኡላህ ነው፡፡ ከኢራን እና ከኢራቅ የስደት እና የእሥር ቤት ህይወት በኋላ የዚህች ምድር የህይወቱ ጉዞ ፍፃሜ የከተናወነው እሥራኤል አገር ሀይፋ የወደብ ከተማ ነው፡፡ ከመወለዳቸው በፊት በውሥጤ ከነበሩ ታላላቅ ሠብዕናዎች አንዱ ባሃኡላህ ነው፡፡ በአሁኑ ሠዓት ከባሃኡላህ መርሆዎች አንዱ የሆነው ዓለም አቀፍ ቤተ ፍትህ International House of Justice የተገነባውና የሚገኘውም በዚህች የወደብ ከተማ ነው፡፡ በአርባ ዓመት የእሥር ቤት ቆይታው ባለ ሠላሣ ሺህ ፅላት ከፍ ባለ እውቀት የተመሉና ባማረ አፃፃፍ የተኳሉ አንድ መቶ አሥር ቅዱሳን መፃህፍት ፅፎአል፡፡ ለአምላክ መልዕክተኛነቱ ማረጋገጫ የሆነው የእግዚአብሔር ክብር (መንፈስ ቅዱስ) በእርሡ ላይ የተገለጠውም እሥር ቤት ውስጥ ሆኖ ነው፡፡ የባሃኢዎች ዋነኛው ቅዱስ መፅሀፍ፡- ኪታብ አል አቅዳስ የሚሰኝ ሲሆን፤ በእርሱ በመልዕክተኛው በባኻኡላህ የተፃፉት የመፃህፍቱ ኦሪጂናል ቨርዢኖች በእሥራኤል ሀይፋ ከተማ ቫኪዩም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቫኪዩም ውስጥ የተደረጉት በዘመናት ብዛት እንዳይበላሹ ታሥቦ ነው፡፡ ወደ አማርኛ ኦሮምኛ ትግሪኛና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች የተተረጐሙ በርካታ የባሃኡላህ መፃህፍት አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ፡- ህቡዓተ ቃላት (The Hidden Words)፤ የባሃኢ ፀሎት፤ ቅስማት፤ ልብን መቀሥቀስ፤ የእርግጠኝነት መፅሀፍ፤ ንገረን (ሶስት ክፍሎች አሉት)፤ ይድረሥ ለተኩላው ልጅ፤ ሠባቱ ሸለቆዎችና አራቱ ሸለቆዎች (The Seven Valleys And The Four Valleys)፤ ባሃኡላህና አዲሱ ዘመን፣ እና ሌሎች በአማርኛ ከተተረጐሙት መፃህፍቱ መሀከል ሊወሡ ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያ የትርጉም ሥራ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ችሎታ የተገለፀባቸው ጭምር ናቸው የባሃኢ መፃህፍት፡፡
የባሃኢ አርማ ባለ ዘጠኝ አውታር ኮከብ ሲሆን፤ እያንዳንዱ አውታር በዓለም ላይ የሚገኝን ሃይማኖት ህልውና ያመላክታል፡፡ ሣቢያን፤ ዞራስተሪያን፤ የአይሁድ እምነት (Judaism)፤ ቡድሂዝም፤ ኢንዱኢዝም፤ ክርሥትና፤ እሥልምና፤ ባቢ፤ የባሃኢ እምነት እነዚህ በሃይማኖቱ ውስጥ እውቅና የተሠጣቸው ዓለም አቀፍ ሃይማኖቶች ናቸው፡፡ አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ፤ የሣይንስና የሃይማኖት ተደጋጋፊነት፤ የመማር ግዴታ፤ የሴቶችና የወንዶች በአጠቃላይ የሠው ልጆች እኩልነት፤ የመላው ዓለም የሰው ልጆች አንድነት፤ ሀይማኖት የፍቅርና የአንድነት መነሻና መሠረት መሆን ያለበት ስለመሆኑ፤ በጐረቤት እውቀት በኩል ሣይሆን በራሥ እውቀት ካለ አንዳች ፕሮጂዲዩስ እውነትን ማየት፤ የዓለም አቀፍ ቤተ ፍትህ አስፈላጊነት፤ የሃይማኖቶች አንድነት፤ በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ጥላ ሥር የመንግሥታትና የአገሮች ህብረት (ድርጅት) አስፈላጊነት … እነዚህ ከባሃኡላህ መሠረታዊ መርሆዎች እዚህ የተወሡት ናቸው፡፡ ከነዚህ መሠረታዊ መርሆዎች፡- ዓለም አቀፍ ቤተ ፍትህ (International House of Justice)፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ሌሎች ተግባራዊ ሆነዋል፡፡
ከምትገድሉ ብትገደሉ ይሻላችኋል፤ እናንተ የአንድ ዛፍ ቅርንጫፎች ናችሁ፤ ለጋዜጠኞች ልባቸውን የተወለወለ መስተዋት አድርገን ዕውቀትን ሠጠናቸው፤ ጠፊው አውሎ ነፋሥ ዘላለማዊውን ሻማ ይፈታተነዋል … የሚለው ባሃኡላህ፡- በዚህች ዓለም ላይ ያለ ህይወቱ ካበቃ በኋላ የባሃኢ እምነትን በሞግዚትነት (በአደራ) የተረከበው አንጋፋ ልጁ አብዱል በሃ ነው፡፡ ባሃኢዎች ባሃኡላህ ወደ ሠማያት አምላክ አርጓል ብለው ያምናሉ፡፡ ግንቦት 21 ቀን May 29 ባሃኡላህ ያረገበት ቀን (Ascension of Behai’u’llah) ተብሎ ይከበራል፡፡ በክርስትና መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ያረጉ፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤሊያስና ሄኖክ ናቸው፡፡
ሠንሠለት ጠንካራ ነው የሚባለው ልል ቀለበት ከሌለው ነው የምትለው ሩሂ ራባኒ የባሀኡላህን አስተምህሮ ካሠረፁ የእርሡ አራተኛ ትውልዶች አንዷ ነች፡፡ ሾጌ ኢፌንዲ ከአብዱል በሀ ቀጥሎ የባሃኡላህ ሶስተኛ ትውልድ ነው፡፡
የባሃኡላህን መከሠት አስቀድሞ ለፋርስ ህዝቦች የገለፀው ግንቦት 15 ቀን May 23 የእግዚአብሔርን ክብር እንደሚመጣ ያወጀው (Declaration of the Bab) ባብ  የተገደለው በአስተሣሰቡ ምክንያት በሰባት መቶ ሃምሣ ጥይት ተደብድቦ ነው፡፡ ወደ መገደያ ቦታ እንውሰድህ ሲሉት ቆይ ሥራዬን ልጨርስ አላቸው፤ ሥራውን ሣይጨርስ ወሰዱና አንድ ባታሊዮን የኢራን ጦር በአንድ ጊዜ ተኮሠበት፡፡ ከተኩሥ በኋላ ባብ ወደነበረበት ሥፍራ ሄደው ቢያዩ አካባቢው በጭስ ከመታፈኑ በቀር አንዳች አጡ፡፡ ባብ ቀድሞ ይሠራ ወደነበረበት ሥፍራ ቢሄዱ ሥራውን እየሠራ አገኙት፤ ሥራውን እንደጨረሰ ወሠዱና አንድ ባታሊዮን ጦር ሠባት መቶ ሃምሣ ጥይት ተኮሰበት፡፡ ይህም ቀን ሀምሌ 2 ቀን July 9 ሲሆን የባብ የሠማዕትነት ቀን Maryrdom of the Bab በመባል ይታወቃል፡፡ የባሃኢ አስተምህሮ ወደ አገራችን የገባው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ባሃኢዎች ማዕከል Bahaai Center በርዕሠ ከ ተማችን አፍሪካ ጐዳና (ቦሌ መንገድ) በተለምዶ ርዋንዳ (ኤምባሲ) እየተባለ በሚታወቀው ሥፍራ ከአሌክሳንደሪያ ህንፃ አጠገብ ይገኛል፡፡ ወደፊት የኢትዮጵያ ባሃኢዎች ቤተ መቅደስ፤ አዲስ አበባን ከከበቧት ስድስት ተራሮች አንዱ በሆነው ፉሪ ላይ የሚገነባ ሲሆን፡- ከኡጋንዳ ካምፓላ ቀጥሎ ሁለተኛው አፍሪቃዊ የባሃኢዎች ቤተ መቅደስ (Ethiopian Bahaai’s Temple) ይሆናል፡፡ ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም በሁለት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን የአገር መሪዎች ሥም ሁለት ዛፍ የተከልኩት እዚህ ቦታ ነው፤ በቴዎድሮስና በመለሥ (መልከ ፀዲቅ) ሥም፡፡ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ክልሎችና ከተሞች የኢትዮጵያውያን ባሃኢ ማዕከሎች ይገኛሉ፡፡
የባሃኢዎች ፆም ከሙስሊም ምዕመናን ፆም ጋር የተመሣሣይነት ባህሪ አለው፡፡ ባሃኢዎች አሥራ ዘጠኙን ቀናት ሙሉ ቀን ምግብ ሳይመገቡ አንዳች ነገር ሳይጠጡ ይውሉና ምሽት ላይ ያሻቸውን ይመገባሉ፡፡ እንዲሁም በዚህ የፆም ወቅት የተቸገሩ ሰዎችን በጣሙን ይረዳሉ፡፡ የባሂኢዎች እርዳታና ድጋፍ ለተረጂው ስሜትና አእምሮ እጅጉን ጥንቁቅ የሆነ ነው፡፡ ተረጂው ይረዳል እንጂ ማን እንደረዳው ላያውቅ ይችላል፡፡ ናውሩዝ ከባሃኢ እምነት ደማቅ ዓመታዊ ክብረ በዓሎች አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ባሃኢዎች በናውሩዝ ዕለት በየፀሎት ማዕከላቸው ተሠባሥበው ባሃኢ ካልሆኑ ወዳጆቻቸው ጋር በዓሉን ያከብራሉ፡፡ የደስታ ቀን (ፊስት) ናውሩዝ በተለይ ለህፃናት ልዩ ትኩረት ይሠጣል፤ በአገራችን በእሥልምናና በክርሥትና ሃይማኖቶች ክብረ በዓላት ቀን ለህፃናት ልዩ ትኩረት እንደሚሠጥ ይታወቃል፡፡ ባሃኢዎች የሠለጠነ ኅብረተሠብ መታያዎች ናቸው፤ የኢትዮጵያ ባሃኢዎች ማዕከል ደግሞ ታላቅ የዕውቀት ባህር ነው፡፡ የየትኛውም ሃይማኖት በመነካትና በመገለጥ የተፃፉ ከፍ ያለ እውቀትና ልቀት ያላቸው ቅዱሣን መፅሀፎትና ሌሎች የጥናትና የምርምር መፃህፍት በዚያ ይገኛሉ፡፡ የባሃኢዎች የፆም ቀናት ከየካቲት 23 እስከ መጋቢት 11 ቀን ምሽት ድረሥ የሚዘልቁ ናቸው፡፡ አገልግሎት በባሃኢ እምነት እንደ ፆም ሊታሠብ ይችላል፡፡ የባሃኢዎች ፆም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ምሽት ይፈሠክና፤ በማግሥቱ ቀኑን ሙሉ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ናውሩዝ [የደስታ ቀን (ፊስት)] ይሆናል፡፡ ባሃኢዎች ባሃኡላህ ብቻ ሣይሆን ሀይማኖቱን በሞግዚትነት የተረከበው አንጋፋ ልጁ አብዱል በሀ ወደ ሰማያት አምላክ አርጓል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህም ቀን አብዱል በሀ ያረገበት ቀን (Ascension of Abdu’l Baha) በመባል በያመቱ ኅዳር 19 ቀን ይከበራል፡፡ በባሃኢ እምነት (Bahaai Faith) ሌሎችም የሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት አሉ፡፡ ይኸውም፡- ኅዳር 3 ቀን የባኻኡላህ የልደት ቀን፤ ጥቅምት 10 ቀን የባብ ልደት ቀን፤ ኅዳር 17 ቀን የቃል ኪዳን ቀን (The day of the Covenant) …  የባሃኢ እምነት፡ በአምላክ የፍቅር ሙላት መተላለፉ ይሰረይለታል እንጂ ማንም ሠው ወደ ሲኦል አይገባም (ሲኦል የለም) ብለው ከሚያምኑ ሃይማኖቶች ጐራ ነው፡፡ በጣም ፃድቁ ሠው በጣሙን ለአምላክ የቀረበው ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ አሜሪካዊው ተመራማሪ ዶክተር ዋይኒ ዳየር Wisdom of the ages በሚል መፅሀፉ ላይ አንድ ፃድቅ ሠው አንድ ኃጢያተኛ ሠው የፅሁፍ ማስታወሻ ተለዋወጡ ይላል፤ ማስታወሻው ሲነበብ፡- ፃድቁ ሠው ኃጢያተኛ ነበር የሚልና፤ ኃጢያተኛው ሠው ፃድቅ ይሆናል (ይቀደሣል) የሚል ነው፡፡
ለአገሬ ለኢትዮጵያ ባሃኢዎች ያለኝን ከፍ ያለ አክብሮትና ልዩ ፍቅር ለመግለፅ በበዛ ፍቅር በከበረ ክብርና እጅግ ከፍ ባለ ትህትና ግሩም ናውሩዝ፡፡
ሠላምዎ ይብዛ! በፍቅር!
Soli. Deo.Gloria!

Read 2714 times