Sunday, 29 January 2017 00:00

የፖለቲካ ጥግ

Written by 
Rate this item
(11 votes)

· በእርግጥ ነፃ ፕሬስ ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን
ይችላል፡፡ ግን ያለጥርጥር ነፃነት በሌለበት
ፕሬሱ መጥፎ ከመሆን በቀር ሌላ ምንም
ሊሆን አይችልም፡፡
አልበርት ካሙ
· በዲሞክራሲያዊ መንግስት ጠንካራ የፍትህ
ሥርዓት ሊኖርህ ይገባል፡፡ የመናገር ነፃነት
ያስፈልጋሃል፡፡ የጥበብ ነጻነትም እንዲሁ፡፡ ነፃ
ፕሬስም የግድ ነው፡፡
ቲዚፒ ሊቭኒ
· ነፃ ፕሬስ የዲሞክራሲ የማዕዘን ድንጋይ ነው፤
ይሄ ምንም አያጠያይቅም፡፡
ሁግ ግራንት
· ነፃ ፕሬስ የተከበረ ፕሬስ ሊሆን ይገባል፡፡
ቶም ስቶፓርድ
· ነፃ ፕሬስን በእጅጉ እደግፋለሁ፤ ነገር ግን
አስተማሪና መረጃ ሰጪ ሊሆን ይገባል፡፡ በዚህ
ረገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሬሱ ወድቋል ብዬ
አምናለሁ፡፡
ሳሙኤል ዳሽ
· ፕሬሱ ዋነኛ የርዕዮተ ዓለም መሳሪያችን ነው፡፡
ኒኪታ ክሩስቼቭ
· የአሜሪካ ህዝብ ፕሬዚዳንቱን በፕሬስ በኩል
ብቻ ሳይሆን በቀጥታ የማየትና አስተያየቱን
የመስማት መብት አለው፡፡
ሪቻርጅ ኤ ም. ኒ ክሰን
· ራስን በማጥፋትና በሰማዕትነት መካከል
ያለው ብቸኛ ልዩነት የፕሬስ ሽፋን ነው፡፡
ቹክ ፓላህኒዩክ
· ብሪቴን በጣም ትንሽ አገር ሆና፣ በጣም ብዙ
ፕሬስ ያላት አገር ናት፡፡
ዴቪድ ሆክኔይ
· ሁሉም ፕሬዚዳንት ፕሬሱን አይወደውም፡፡
ሔለን ቶማስ
· እውነቱን ለመናገር ፕሬሱን አላነብም፡፡ ምን
እያሉ እንደሆነ አላውቅም፡፡
ሴሬና ዊሊያምስ
· የፕሬስ ነጻነት የተረጋገጠው የፕሬስ ባለቤት
ለሆኑቱ ብቻ ነው፡፡
ኤ.ጄ.ላይብሊንግ  

Read 3484 times