(ትውልደ ቼክ የብሪቲሽ ፀሃፌ ተውኔትና የስክሪፕት ፀሃፊ)
አንዳንድ ጓዶች ዲሞክራሲ መፈክር ብቻ መሆኑን ለመረዳት ተቸግረዋል፡፡
ሚኻኤል ጐርባቾቭ
(የሩሲያ መሪ የነበሩ)
ዲሞክራሲ፤ ውክልና የተሰጠው መንግስት የሚባል አደገኛ ቀልድ ነው፡፡
ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ
(የብሪቲሽ ጠ/ሚኒስትርና ፀሃፊ)
የህዝቡ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፡፡
ከማል አታቱርክ
(የቱርክ መሪ የነበሩ)
የምዕራባውያን ዲሞክራሲ በውስጡ የህይወትን ፍሬ የያዘ ቢመስልም በታሪካችን ውስጥ ከሞት ፍሬም ጋር የተገናኘ ነው፡፡
ፋቲማ ሜርኒሲ
(የሞሮኮ ፀሃፊ)
ፋሺዝም ሃይማኖት ነው፤ 20ኛው ክ/ዘመን በታሪክ ውስጥ የፋሺዝም ክ/ዘመን ተብሎ ይታወቃል፡፡
ቤኒቶ ሙሶሎኒ
(የጣሊያን አምባገነን መሪ የነበሩ)
ፋሺዝም በራሱ አዲስ የማህበረሰብ ስርዓት አይደለም፡፡ አልወለደም ያለ መጪው ዘመን እንጂ፡፡
አኔዩሪን ቤቫን
(የብሪቲሽ ፖለቲከኛ)
በፖለቲካ ውስጥ፣ ምንም ነገር እንዲባል ከፈለግህ ወንድን ጠይቅ፤ ምንም ነገር እንዲሰራ ከፈለግህ ግን ሴትን ጠይቅ፡፡
ማርጋሬት ታቸር
(የብሪቲሽ ጠ/ሚኒስትር የነበሩ)
ከአገርህ ውጪ ከሆንክ መንግስትህን አትተች፤ አገር ውስጥ ከሆንክ ደሞ ከመተቸት ወደ ኋላ አትበል፡፡
ዊንስተን ቸርቺል
(የብሪቲሽ ጠ/ሚኒስትርና ፀሃፊ የነበሩ)
ዛሬ ለእኔ ድምፅ ከሆናችሁልኝ፣ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የናንተ ድምፅ እሆንላችኋለሁ፡፡
ቢል ክሊንተን
(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ - በምርጫ ቀን ተናገሩት)