Print this page
Saturday, 15 October 2016 12:37

ሀገር

Written by  ጋሻው ሙሉ
Rate this item
(10 votes)

በህብር፣ በደቦ፣ ባንድ ተደጉሶ
ከተመሰረተ ከቆመ ምሰሶ
ጥራናው ተጥሎ ከዞረ ማቶቱ
ጠብቆ ከታሰረ ከላይ ጉልላቱ
አንድም የሳር ክዳን ሰበዝ ካልመዘዙ
ማገር ከማገሩ፣ ዙሪያ ካጠበቁ፣ አብረው፣ ከተጓዙ
በፍቅር ከዋሉ በፍቅር ካደሩ
ባንድ እጅ ከበሉ ባንድ ከዘመሩ
ዳስ፣ ድንኳን ተጥሎ «በእልልታ» ታጅቦ
ጉተና ተነቅሶ፣ ጃኖ ተደርቦ፣ ብሎ «ሎጋው ሽቦ»
ሀገር ይሞሸራል!!!
ሀገርም ይዳራል!!!
ሀገርም ይኳላል!!!
ሀገርም ያገባል!!!፡፡


Read 3803 times